Stationery
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሠላም ፀጥታ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ስቴሽነሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሠላም ፀጥታ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ስቴሽነሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ተጫራቾች፡-
- የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል
- የንግድ ሥራ ፈቃድ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል
- በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል
- በአቅራቢነት በጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከመንግስት መ/ቤት የተሰጠ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ እና ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ሁሉም ዶክሜንት ላይ የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍና በመፈረም በሰም ለየብቻቸው አሽጎ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ 10,000 (አስር ሺህ) ብር CPO (ሲ.ፒ.ኦ) በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ስም በማሰራት ብቻውን በሰም አሽጎ ማስያዝ የሚችል
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸው በተገለጸበት በ5 (አምስት) ቀን ውስጥ ውል መፈጸም እና የውል ማስከበሪያ ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ CPO (ሲ.ፒ.ኦ) ማስያዝ የሚችል ማንኛውንም ወጪዎች ማለትም የጉምሩክ የትራንስፖርት የባንከ እና የሌሎች አገልግሎት ሰጪዎችን በራሱ ሸፍኖ ዕቃውን ማስረከብ የሚችል ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ) ብር ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሠላም ፀጥታ ቢሮ ግዥ/ፋይ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 507 ቀርበው በመክፈል ሰነዱን በመውሰድ በተዘጋጀው የጨረታ ሠነዱ ላይ የአንዱን እና ጠቅላላ ዋጋ በመሙላት ፖስታውን አሽጎ : ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ተከታታይ በ15 ሥራ ቀናት ውስጥ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሠላም ፀጥታ ቢሮ ግቢ ውስጥ ግዥ/ፋይ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮው ቁጥር 507 ባለው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሳጥን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዛው ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡-
- መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ሌላው ተጫራች ተንተርሶ ማጫረት አይችልም
- የወቅቱን የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም ከቀረበም የዋጋ ትንታኔ መያያዝ አለበት
- ጨረታው የሚከፈተው በሥራ ቀን ካልዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን ይሆናል።
- ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 046 212 5731 ደውለው ማረጋገጥ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሠላምና ፀጥታ ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-10-05
- Bid closing time: 15:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-05 15:30
- Bid opening (note): ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Sidama National Regional State Peace and Security Office
- Bid bond: 10,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Sep 17, 2026)
- Posted at: 2026-09-17T08:32:01.000Z
- Source: 2merkato