Stationery

በጉለሌ ክ/ከተማ ቱፋ ሙና ቅ/አ አንደኛ እና መ/ደ/ት/ቤት ልዩ ልዩ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን በመጀመሪያ ዙር ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 001/2019

በጉለሌ ክ/ከተማ ቱፋ ሙና ቅ/አ አንደኛ እና መ/ደ/ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ፣ ድጎማ እና በውስጥ ገቢ በጀት የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን በመጀመሪያ ዙር ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት1 የፅህፈት መሳሪያ
  • ሎት2 የደንብ ልብስ፣
  • ሎት3 የደንብ ልብስ ማሰፊያ
  • ሎት 4 አጋዥ መፅሐፍት
  • ሎት5 የፅዳት እቃዎች ፣
  • ሎት6 የኤሌትሪክ እቃዎች
  • ሎት7 የኮምፒውተርና፣ፕሪንተር ጥገና
  • ሎት8የህትመት ስራዎች፣
  • ሎት 9 ቋሚ እቃዎች
  • ሎት10 የጥገና ስራ
  • ሎት11 የካፌ አገልግሎት ግዥ
  • ሎት12 የጭነት አገልግሎት እና
  • ሎት13 የአላቂ የትምህርት እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች መወዳደር ትችላላችሁ።

1. የንግድ ምዝገባ፣በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ መለያ ቁጥር (TIN) የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላችሁና የተጨማሪ እሴት ታክስ /vat 15%/ ተመዝጋቢ የሆናችሁ።

2. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች እና አገልግሎቶች ዋጋውን ከነቫቱ መሙላት ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4 ተወዳዳሪዎች ለሚወዳደሩባቸው አቅርቦቶች ናሙና ማቅረብ የሚችሉ።

5. አንዱ በሌላው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 10,000 /አስር ሺህ/ ለሎት 2 ብር 12,000.00 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ ለሎት 3 ብር 2,000.00 /ሁለት ሺህ ብር / ለሎት 4 ብር 5,000.00/ አምስት ሺህ ብር /ለሎት5 2,000.00 /ሁለት ሺህ ብር/ ለሎት 6 ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ ለሎት 7 ብር 1,000.00 ብር /አንድ ሺህ ብር/ ለሎት 8 ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር ለሎት 9 ብር 12,000.00 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ ለሎት 10 ብር 12,000.00 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ ለሎት 11 12,000.00 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ ለሎት ብር 12,000.00 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ 13 እና ለሎት ብር 5,000.00 ብር አምስት ሺህ በባንከ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው። እንዲሁም ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆነ ልዩ አስተያየት የሚኖረው አምራች በሆኑበት እቃዎች ላይ ብቻ ከአደራጃችሁ አካል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባችኋል።

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የመንግስት የስራ ቀን ድረስ ከቢሮ ቁጥር 3 ግዥ ከፍል በመምጣት በመንግስት የስራ ሰዓት በእያንዳንዱ የጨረታ አይነቶች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዋጋ በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል መውሰድ ይችላሉ።

8. ተጫራቾች ሰነዱን በመሙላት ኦርጅናል የፋይናንሺያል እና የቴክኒኩን በአንድ ፖስታ እና ኮፒውን በሁለት ፖስታ በማሸግ እስከ 10ኛው የመንግስት የስራ ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመንግስት የስራ ሰዓት በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 7 ቱፋ ሙና ቅ/አ/አንደኛ እና መ/ደ/ት/ቤት በቢሮ ቁጥር 3 ፋይናንስ ክፍል ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

9. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ10ኛው ቀን 11:30 ሠዓት ላይ ታሽጎ በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 3፡30 ላይ በቢሮ ቁጥር 3 ፋይናንስ ክፍል ውስጥ ይከፈታል።

10. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ቱፋ ሙና ቅ/አ/አንደኛ እና መ/ደ/ት/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለባቸው::

11. መስሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ናሙናዎችን ቀድመው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

13. መስሪያ ቤቱ አሸናፊ ተጫራቾችን ከመረጠ በኋላ ለሚገዙት እቃዎች ብዛት መጠን ላይ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 20% የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ የዋጋ ለውጥም ሆነ ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም። በተወዳደሩበት ዋጋ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው ከ7(ሰባት) የቅሬታ ቀን በኋላ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 2 ቀርበው የውል ማስከበሪያ 10% ለግዥ ፈፃሚው አካል ማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል። ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው በውሉ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ከተወጡ ያስያዙት የውል ማስከበሪያ ተመላሽ የሚደረግ ይሆናል።

አድራሻችን፡- ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 በሱሉልታ በር ወደ እንጦጦ ማርያም /እንጦጦ ፓርክ በሚወስደው መንገድ 350 ሜትር ገባ ብሎ ቱፋ ሙና ቅ/አ/አንደኛ እና መ/ደ/ት/ቤት ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011-819-6682

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ቱፋ ሙና ቀ/አ/አንደኛ እና መ/ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-28
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 11:30 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-09-29 09:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 3፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Tufa Muna Elementary and Primary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Sep 17, 2026)
  • Posted at: 2026-09-17T08:47:19.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders