Building and Finishing Materials

አዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን: የግንባታ እቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

Please click on this Link In order to Bid on the Electronic Government Procurement website

https://production.egp.gov.et/egp/bids/all/tendering/16bc965e-7db8-442e-8985-39bccb5e1f4c/open

Invitation to Bid

“የግንባታ እቃዎች ግዥ”

Procurement Reference No: AACRA-NCB-G-0031-2019-BID-Open
Procurement Category: Goods

Market Type: National
Procurement Method: Open

Procurement Classification Code: 

  • Code: 13000000
  • Title: Resin and Rosin and Rubber and Foam and Film and Elastomeric Materials


Lot Information 

  • Object of Procurement: የግንባታ እቃዎች ግዥ
  • Description: Asphalt Hot Mix (Wearing and Binder Course)
  • Lot Number: 1
  • Clarification Request Deadline: Sep 22, 2026, 5:00:00 PM
  • Pre-Bid Conference Schedule: Not Applicable
  • Site Visit Schedule: Not Applicable
  • Bid Submission Deadline: Oct 2, 2026, 11:00:00 AM
  • Bid Opening Schedule: Oct 2, 2026, 12:00:00 PM

Eligibility Requirements
Participation Fee:
  
Eligibility Documents: 

Financial Qualification

Factor Criteria
የፋይናንስ አቅም

በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሰንጠረዥ ንዑስ አንቀጽ 15.2 (ለ) መሰረት ተጫራቾች ይህን ውል በተገቢው መንገድ ለማከናወን በቂ የፋይናንስ አቅም ያላቸው መሆኑን በሚያሳይ መልኩ የጨረታ ዝርዝር መረጃ ሰንጠረዥ በሚያዘው መሰረት በክፍል 4 የተመለከተውን የተጫራቾች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ወይም ይህን ውል ለማከናወን የሚያስችል የፋይናንስ ድጋፍ የብድር ስምምነት ከታወቀ ባንክ ቢያንስ 50 ሚሊዮን ብር በማቅረብ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ወይም የፋይናንስ አቅማቸውን የሚያሳይ ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ የሂሳብ መግለጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

የኦዲት ሪፖርት

ተጫራቾች በቂ የሆነ የፋይናንስ አቅም ያላቸው መሆኑን የሚያሳይ በገለልተኛ ኦዲተር የተረጋገጠ ያለፉት 2 ዓመታት የኦዲት ሪፖርት ማቅረብ አለባቸው፡፡

Legal Qualification

Factor Criteria
የታደሰ የንግድ ፈቃድ

በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.6 (ለ) (i) መሠረት ተጫራቹ ከሥራው ጋር አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ሳይችል ሲቀር፣

የንግድ ምዝገባ ሰርቲፊኬት ወይም የንግድ ፈቃድ

በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.6 (ሐ) መሠረት የውጭ ሀገር ተጫራች ሆኖ ከተቋቋመበት ሀገር የንግድ ምዝገባ ሰርቲፊኬት ማቅረብ ሳይችል ሲቀር፣

የተጨማሪ እሴት የምዝገባ ሰርቲፊኬት

በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሠንጠረዥና በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.6 (ለ) (ii) መሠረት የሀገር ውስጥ ተጫራች ሆኖ በታክስ ባለሥልጣን የተሰጠ የተጨማሪ እሴት ታከለ የምዝገባ ሰርቲፊኬት ማቅረብ ሳይችል ሲቀር፣ 

ታክስ የከፈለበትን ሰርቲፊኬት

በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.6 (ለ) (iii) መሠረት የሀገር ውስጥ ተጫራች ሆኖ ታክስ የከፈለበትን ሰርቲፊኬት ከታክስ ባለሥልጣን ማቅረብ ሳይችል ሲቀር፣

Performance Qualification

Factor Criteria
አፈጻጸም

ማንኛውም ተጫራች ባለፉት 2 ዓመታት ውስጥ ከባለስልጣን መ/ቤቱ ጋር በአግባቡ ያልፈጸመው ውል ካለው ወይም በእያንዳንዱ በዚህ ጨረታ በቀረበው ምርት ዓይነት ውል ኖሮት ደካማ አፈጻጸም ያለው በግልግል ወይም አስተዳደራዊ ውሳኔ የተሰጠው ተጫራች በዚህ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ 

ከዚህ በፊት የነበረን ዉል በተመለከተ

በዚህ ጨረታ መሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች በ2018 በጀት አመት የተመሳሳይ ግብዓት ዓይነት ውል ኖሯቸው ከ80 በመቶ (80%) በላይ አጥጋቢ አፈፃፀም ሊኖራቸው ይገባል፡፡

ከዚህ በፊት የነበረን ዉል ቀሪ አፈፃፀምን በተመለከተ

ከ80% በላይ አጥጋቢ አፈፃፀም ኖሯቸው የጨረታ አሸናፊ ቢሆኑ አቅርቦት ለመጀመር የቀድሞውን ውለታ በሚገባ ማጠናቀቅ እንደሚችሉ በፅሁፍ ማረጋገጫ መስጠት ይኖርባቸዋል ፡፡

Technical Qualification

Factor Criteria
የባለቤትነት ማረጋገጫ

ተጫራቾች የራሳቸው የሆነ የአስፋልት ማምረቻ ፕላንት፣ክሬሸር እና ኳሪ ሊኖራቸው ይገባል፡፡የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ሊብሬ እንዲሁም በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ ውክልና ወይም ለዚህ ጨረታ የአቅርቦት ጊዜ የሚሸፍን የኪራይ ውል ለውል ዘመኑ የሰነድ ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ማረጋገጫ ያላቀረበ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡

ዲዛይን ሚክስ እና ላብራቶር ፍተሻ

ተጫራቾች የሚያቀርቡት ምርት በክፍል 6 በተገለፀው የቴክኒክ ፍላጎት መግለጫ መሰረት መሆኑን የሚያረጋግጥ ከታወቀ ላብራቶሪ ማዕከል ወይም በሌላ 3ኛ ወገን አማካሪ የተረጋገጠ የላብራቶሪ ፍተሻ ዉሳኔ እና ሚክስ ዲዛይን ዶክመንት ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ሰነዱ ከተዘጋጀ 6 ወር መብለጥ የለበትም፤ የቀረበው ዶክመንት ክፍል 6 የተቀመጠው የጥራት መግለጫ ማሟላት አለበት

ማሽኑ ካሊቢሬት የተደረገበት ህጋዊ ሰነድ

ለሚቀርበዉ ማሽን ካልብሬት የተደረገበት ህጋዊ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው እነዚህን ሰነዶች ማቅረብ ያልቻለ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡ 

አቅርቦትን በተመለከተ

አሸናፊ ተጫራቾች ውል ከተዋዋሉበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ የእያንዳንዱን ሎት ቢያንስ በቀን 600 ቶን በቀንም ሆነ በማታ የስራ ሸፍት ማቅረብ ይኖርበታል እንደ አስፈላጊነቱ ፍላጎቱ እስከ ሚጠናቀቅ ድረስ ባለስልጣን መ/ቤቱ በሚያቀርበው ጥያቄ መሰረት ከ600 ቶን በላይ በቀንም ሆነ በማታ የስራ ሸፍት ማዘዝ ይቻላል፡፡ ተጫራቹ ስምምነቱን በፅሁፍ ከቴክኒክ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለበት::

የአስፋልት ፕላንት አቅም

ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የሚያቀርቡት የአስፋልት ፕላንት ሰነድ በቀን 1000 ቶን እና ከዛ በላይ የማምረት አቅም ሊኖረዉ የገባል፡፡

በሁለቱም ሎት ለመወዳዳር በቀን 1000 ቶን እና ከዛ በላይ ማምረት የሚችሉ ሁለት ፕላንት ሊኖረው ይገባል ይህንንም ተጫራቹ ስምምነቱን በፅሁፍ ከቴክኒክ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡ለዚህም የሰነድ ማረጋገጫ ማቅረብ አለበት፡፡

GPS በተመለከተ

ተጫራቾች የግብዓት ምርት አቅርቦት የሚያከናውኑበት ተሸከርካሪዎች በራሱ ወጪ ጂፒኤስ (GPS) በማስገጠም የማቅረብ ግዴታ አለበት የGPS ሥርዓቱ በባለስልጣኑ መሥሪያ ቤት በተመደቡ ባለሙያዎች የቀጥታ እና የቅርብ ክትትል እንዲደረግበት የሚያስችል ሲሆን፣ አቅራቢው የሥርዓቱን Username እና Password ለባለስልጣን መ/ቤት መስጠት ይኖርበታል።ለዚህም ተጫራቹ ስምምነቱን በፅሁፍ ከቴክኒክ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡

የክብደት ልኬት

ተጫራች በእያንዳንዱ ጭነት ለሚቀርበው ምርት ክብደት መጠን መለካት ያለበት ሲሆን በማምረቻው ቦታ የምድር ሚዛን ወይም control Room print out ያለው መሆኑን በጽሑፍ ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡ የምድር ሚዛን ወይም control Room print out የሌለው ወይም የጽሑፍ ማረጋገጫ ያላቀረበ ተጫራች በቴክኒክ ግምገማ ወቅት ከጨረታ ውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡

የፍላጎት መግለጫ(specification)

ተጫራቾች በክፍል 6 በPDF በተቀመጠው ፍላጎት መግለጫ መሰረት ስፔሲፊኬሽናቸውን ማቅረብ አለባቸው 

Bid Security Amount: 500,000 ETB

Bid Security Form For MSE: Letter from Small and Micro Enterprise,

Bid Security Form For Local Bidders: CPO, Bank_Guarantee,

Bid Security From for Foreign Bidders: Bank_Guarantee, CPO,

Notice: 

  • Terms and Conditions: ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጫራጮች ኪይ(key share)ማድረግ አለባቸው፡፡

Address: 

  • Procuring Entity: Addis Ababa Road Authority
  • Country: Ethiopia
  • Town: Addis Ababa
  • Street: pushkin
  • Room Number: 1st
  • Telephone: +251113714103
  • Email: [email protected] 
  • Po Box: 9206
  • Fax: 1000

Tender details

  • Deadline: 2026-10-02
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid opening: 2026-10-02 12:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Road Authority
  • Bid bond: 500,000 ETB
  • Published on: Government (Sep 18, 2026)
  • Posted at: 2026-09-18T06:47:21.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders