Stationery

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ባቲ ከተማ አስተዳደር ገን/ጽ/ቤት ለባቲ ከ/አስ ለሁሉም ሴክተር ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የፅህፈት መሳሪያ፣ የፅዳት እቃ እና የላንድ ክሮዘር መለዋወጫ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ባቲ ከተማ አስተዳደር ገን/ጽ/ቤት ለባቲ ከ/አስ ለሁሉም ሴክተር ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ማለትም

  • ሎት 1.የፅህፈት መሳሪያ
  • ሎት 2.የፅዳት እቃ
  • ሎት 3.የላንድ ክሮዘር መለዋዎጫ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-

1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ተጫራቾች የንግድ ፈቃዳቸው በጀርባው የሚገልፅ ካለው ኮፒ አድርገው ያያይዙ።

2. የግብር መለያ ቁጥር ወይም TIN NO ተመዝጋቢ የሆኑ።

3. ተጫራቾች እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁ.1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ አድርጎ ማቅረብ የሚችል።

5. የሚገዙ እቃዎችን እይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለሰ 200 ብር በመክፈል ሰነዱን ቢሮ ቁ.6 ከዋና ገ/ያዥ ላይ መግዛት ይችላሉ፡፡ የሚወዳደሩበት ሰነድ የያዘው ፖስታ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩት ቁርጥ ዋጋ ሎት 1.የፅህፈት መሳሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ሎት 2.የፅዳት እቃዎች 6,000 (ስድስት ሺህ ብር) ሎት 3.የላንድ ክሮዘር መለዋዎጫ 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ ወይም cpo ወይም ቢድ ቦንድ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባቲ ከተማ አስ/ ገን/ጽ/ቤት በመሂ1. ገቢ አድርጎ ከዋና ጨረታ ሰነድ ጋር ፖስታ ውስጥ አስገብተው ማቅረብ አለባቸው፤ በእጅ cpo ወይም ጥሬ ገንዘብ ይዞ መቅረብ አይቻልም።

7. ይህ ግልጽ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ10 ቀን ማለትም 8/1/2019 እስከ 17/1/2019 የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ከጽ/ቤቱ ዋና ገንዘብ ያዥ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

8. ይህ ግልጽ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 11ኛው ቀን ላይ በ18/1/2019 ዓ.ም በ3፡30 ሁሉም ሳጥን ታሽጎ በዚሁ ቀን ሎት 1 ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ፣ ሎት 2 ከጠዋቱ 5፡00 ፣ ሎት 3 ከጠዋቱ 6፡00 ሰአት ላይ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው ሲከፈት ሳይገኙ ቢቀሩ ጨረታውን ከመክፈትም ሆነ በጨረታውን ሂደት ለሚወስኑ ውሳኔዎች ተገዥ ናቸው።

 9. ጨረታውን መ/ቤቱ በሎት ድምር ማወዳደር እንደሚችል ታውቆ በሰነዱ ላይ የተዘረዘሩት እቃዎች ሁሉ ዋጋቸው መሟላት አለባቸው፡፡ ሳይሞሉ የቀሩ ካሉ ከጨረታ ውጭ ውድቅ ይደረጋል።

10. አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች በባቲ ከ/አስ/ ስር ባሉት 4 ንብረት ክፍል ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

11. በባለሙያ መታየት ያለባቸው እቃዎችን ጽ/ቤቱ በሚያቀርበው ባለሙያ አረጋግጠን የምንረከብ መሆኑን ተጫራቾች ማወቅ አለባቸው።

12. የእቃ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ በመጠቀም በተገለጸው ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ መሰረት መሞላት ይኖርበታል ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከተቀየረ ውድቅ ይደረጋል፣ እንዲሁም ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ ተለይቶ በዝርዝር በመሙላት የድረጅቱን ስም፣ ቀን በመፃፍ በመፈረምና በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ስርዝ ድልዝ ካለ ከጨረታ ውጭ ይሆናል ይደረጋል።

13. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ይህ ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለማወዳደር እና ላወጡት ወጪ መቱ ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑን እንገልፃለን።

14. መ/ቤቱ 20% የመቀነስ እና የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ የጨረታ ሳጥኑ በቀጣዩ የስራ ቀን ታሽጎ የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0910192412 ወይም 0920780412 መደወል ይችላሉ።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ባቲ ከተማ አስተዳደር ገን/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-28
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): በ18/1/2019 ዓ.ም በ3፡30
  • Bid opening: 2026-09-28 12:00
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Bati City Administration FEDB
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Sep 18, 2026)
  • Posted at: 2026-09-18T08:42:29.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders