Printing and Publishing
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስፖርት ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት ለስፖርት ምክር ቤት ግቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ግዥ እንዲሁም ለሀገረ-ሰላም አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 60 ለሰልጣኞች የምግብ አቅርቦት በድጋሚ በማውጣት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስፖርት ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት ለስፖርት ኮሚሽን
- ሎት 1 ለስፖርት ምክር ቤት ግቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ግዥ ፣
- ሎት 2 ለሀገረ-ሰላም አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 60 ለሰልጣኞች የምግብ አቅርቦት በድጋሚ በማውጣት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች፣
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) እየከፈሉ ከመ/ቤቱ ግዢ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን 10,000 (አስር ሺህ) በጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ጨረታው በሁለት ፖስታ የሚቀርብ ሲሆን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ መቅረብ አለበት። ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 15ተኛው ከቀኑ 10:00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ በ10፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ16ኛው ቀን 4፡00 የሚከፈት ይሆናል።
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ስማቸውንና ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውንና ስልክ ቁጥር ማስፈር አለባቸው።
7. መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ የግዥውን ብዛት መጠን/ እንደአስፈላጊነቱ እስከ 20% ለመቀነስ |ለመጨመር) መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የደረሰኝ አይነት እና ምግብ አይነት መ/ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን ዝርዝር መሰረት ብቻ ነው መወዳደር የሚችሉት።
9. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡-
046 221 6730/0919 155 930 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
የመ/ቤቱ አድራሻ ሀዋሳ ከተማ ቀድሞ ሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ቅጥር ግቢ።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስፖርት ኮሚሽን
Tender details
- Deadline: 2026-10-02
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ተኛው ከቀኑ 10:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-03 10:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00
- Region: Sidama
- Publishing entity: Sidama National Regional State Sport Commission
- Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 18, 2026)
- Posted at: 2026-09-18T09:03:40.000Z
- Source: 2merkato