Building Construction
ገነት ሆቴል በግቢው ውስጥ ያሉትን ነባር የመጸዳጃ እና መታጠቢያ ክፍሎች የግንባታ እድሳት ስራን ለማሰራት ብቁ የሆኑ የሀገር በቀል የህንጻ ወይም የጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃ- 5(አምስት) እና ከዚያ በላይ የሆኑ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል
Description
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የነባር መጸዳጃ እና መታጠቢያ ክፍሎች የእድሳት ስራ
ገነት ሆቴል በግቢው ውስጥ ያሉትን ነባር የመጸዳጃ እና መታጠቢያ ክፍሎች የግንባታ እድሳት ስራን ለማሰራት ብቁ የሆኑ የሀገር በቀል የህንጻ ወይም የጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃ- 5(አምስት) እና ከዚያ በላይ የሆኑ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች እንዲሁም የሰው ኃይል፣ ማሽን እና የግንባታ ግብዓቶችን ማሟላት የሚችሉ ስራ ተቋራጮች ስራውን ለማከናወን በግልፅ ጨረታ ውድድር መሳተፍ ይችላሉ።
- በህንጻ ወይም በጠቅላላ ስራ ተቋራጭነት ደረጃ -5(አምስት) እና ከዚያ በላይ ሆነው የታደሰ ፍቃድ ያላቸው።
- የ2018/19 ዓ.ም ዘመን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ ሰርተፍኬት(VAT) ያላቸው።
- የግብር ከፋይ ምዝገባና ሰርተፍኬትና መለያ ቁጥር (TIN) ሰነድ ያላቸው።
- በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ፍቃድ ያላቸው።
- ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ታሳቢ የሚደርግ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ ከድርጅታችን የፋይናስ ቢሮ ክፍል የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 80,000.00 (ሰማንያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ለ”ገነት ሆቴል” በሚል በማሰራት ከቴክኒካል ሰነድ ጋር ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሻል ሰነድ ለእያንዳንዳቸው አንድ ኮፒ በማዘጋጀት በተናጥል ለየብቻ በማሸግ በጥቅል በአንድ በሰም በታሸገ ፖስታ በማደረግ እስከ አስራ አምስተኛው (15) ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የፋይናንስ ክፍል ቢሮ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤ አስራ አምስተኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ የጨረታው መክፈቻ ቀጣይ ባለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ተወካዮች ባሉበት በአስራ አምስተኛ (15) ከቀኑ 9፡00 በድርጅቱ አዳራሽ ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አ/አ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ካሳ ግራንድ ሞል ፊት ለፊት
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- 0115-504 701/0911-250 641/0939–500000
ገነት ሆቴል
Tender details
- Deadline: 2026-10-02
- Bid closing time: 14:30
- Bid closing (note): የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስራ አምስተኛው (15) ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-02 15:00
- Bid opening (note): የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስተኛ (15) ከቀኑ 9፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Genet Hotel Enterprise
- Bid bond: 80,000 (ሰማንያ ሺህ ብር)
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 18, 2026)
- Posted at: 2026-09-18T09:07:07.000Z
- Source: 2merkato