Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ወለጋ ዞን የስቡ ሲሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዘመን በወረዳው ውስጥ ለሚገኙት የመንግስት መ/ቤቶች የሚያስፈልጉ ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽህፈት መሣሪያዎችን፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮንክሶች፣ ፈርኒቸር፣ የመኪና ጎማዎች፣ የደንብ ልበስ እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 003/CI/2019
በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ወለጋ ዞን የስቡ ሲሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዘመን በወረዳው ውስጥ ለሚገኙት የመንግስት መ/ቤቶች የሚያስፈልጉ ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች የጽህፈት መሣሪያዎችን፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮንክሶች፣ ፈርኒቸር፣ የመኪና ጎማዎች፣ የደንብ ልበስ እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታማሉ ድርጅቶች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን።
1. ተጫራቾች የ2019 የታደሠ እና አግባብነት ያለው ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸውና የ2018 ዘመን ግብር የከፈሉ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
2. ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ካርድ “TIN card" ያላቸውና ማስረጃ የሚያቀርቡ።
4. ለመንግስት መስራቤቶች በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው።
5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ከስቡ ሲሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ለሠነዱ የማይመለስ ብር 1000(አንድ ሺህ) ከፍለው በመግዛት የዋጋ ማቅረቢያቸውን ሰነድ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፕ በተለያዩ በሁለት ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማቅረብ በስቡ ሲሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ የ100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ)ብር CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7. አሸናፊው ተጫራች ውል ሲፈርም በተፈራረመው ብር መጠን የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO 10% ማሲያዝ አለበት።
8. አሸናፊ የሆኑት ተጫራቾች በእስፔስፍኬሽኑ መሰረት ጥራቱን የጠበቀ ዕቃ እና በተባለው ጊዜ ውስጥ ለማቅረብ ማሸነፉን የሚገልጽ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 5(አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ በስቡ ሲሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ከመስሪያቤቱ ጋር ውል የመፈረም ግዴታ አለበት።
9. አሸናፊ የሆኑት ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ እስከ ስቡ ሲሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ የሚችል።
10. መስሪያ ቤቱ የሚገዛውን የዕቃ ብዛት በ20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ተኛው የስራ ቀን ወይም 29/1/2019 ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት የሚታሸግ ሆኖ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግልጽ የሚከፈት ሆኖ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ለመከፈት የማያግድ መሆኑን እናሳውቃለን።
12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 12 00 12 54 / 09 11 79 58 87
በምሥራቅ ወለጋ ዞን የስቡ ሲሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-09
- Bid closing time: 09:30
- Bid opening: 2026-10-09 10:00
- Region: Oromia
- Publishing entity: East Wellega Zone Sebu Sire Woreda FEDB
- Buyer address: የስቡ ስሬ ወረዳ ዋና ከተማ ስሬ ከአዲ አበባ ወረዳ ነቀምቴ በሚወስደው የአስፋልት መንገድ 280 ኪ.ሜ ላይ ትገኛለች፡፡
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 1,000.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 18, 2026)
- Posted at: 2026-09-18T09:40:17.000Z
- Source: 2merkato