Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በደቡብ ኢትዮጵያ ከልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በጎፋ ዞን የሣውላ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም በ2019 ዓ/ም የፅህፈት መሣሪያ፣ የፅዳት ዕቃ እና የትምህርት ቁሳቁስ አገልግሎት የሚውል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ከልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በጎፋ ዞን የሣውላ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም በ2019 ዓ/ም የፅህፈት መሣሪያ፣ የፅዳት ዕቃ እና የትምህርት ቁሳቁስ አገልግሎት የሚውል፡- በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች መስፈሪቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያለው።

2. የዘመኑን ግብር የከፈለ።

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ።

4. የግብር መለያ /Tin/ ቁጥር ያለው።

5. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስከር ወርቀት ማቅረብ የሚችሉ።

6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በCPO የተረጋገጠ 50,000.00/ሃምሳ ሺህ ብር/ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች ከ1 እስከ 5 የተጠቀሰውን ማስረጃዎችን እና የማጫረቻ ሠነድ ኦርጅናልና ኮፕ በተለያዩ ፖስታ ውስጥ በማስገባት በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በመንግስት የሥራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው።

8, የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመንግስት የሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ የማይመለስ 300/ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሠነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

9. ተጫራቾች ዕቃውን በራሳቸው ወጪ እስከ ሣውላ ማረሚያ ተቋም ግቢ አምጥተው ማስረከብ አለባቸው።

10. የጨረታው አሸናፊ ሆነው የተገኙ ተጫራች የዕቃዎችን አጠቃላይ ዋጋ በ10% በባንከ የተረጋገጠ ቼክ ወይም /Cpo/የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከሣውላ ማረሚያ ተቋም ግዥ ፋን/አስ/ር ደጋፊ ሥራ ሂደት ጋር የውል ስምምነት መፈፀም ይጠበቅባቸዋል።

11. ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ከሁሉም ዓይነት ናሙና ይዘው መቅረብ አለባቸው።

12, የጨረታ ማስታወቂያ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሳጥን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ዕለቱ በ4፡30 ላይ ተጫረቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። ዕለቱ ቅዳሜ እሁድ እና በዓል ቀን ከሆነ በምቀጥለዉ ቀን በመንግሰት ሥራ ሰዓት ይከፈታል።

13. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መወዳደር ተቀባይነት የለውም።

14. ማረሚያ ተቋሙ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 16 47 99 09 / 09 16 87 73 79

የሣውላ ማረሚያ ተቋም የግዥ ፋ/ን/አስ/ር ደጋፊ ሥራ ሂደት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-03
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-03 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Sawula Correctional Facility
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 18, 2026)
  • Posted at: 2026-09-18T09:42:09.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders