Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የቡልጋ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት ጥቅል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02/19

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የቡልጋ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት ጥቅል ግዥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡-

ስለዚህ ተጫራቾች፡-

  • ሎት 1 የጽሕፈት መሣሪያ
  • ሎት 2 ቋሚ አላቂ 
  • ሎት 3. የፅዳት እቃ
  • ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ
  • ሎት 5. ፈርኒቸር
  • ሎት 6 የመኪና ጐማ

1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው እና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት በአቅራቢነት ማስረጃ ያላቸው

3. ግዥውን ለመሳተፍ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከርነት ወረቀት እና የታክስ ክሪላንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. የሚገዙ እቃዎችን አይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊክሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግዥና ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ማግኘት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ለጽሕፈት መሣሪያ 17ዐዐዐ ብር፣ ለቋሚ አላቂ 2500 ብር፣ ለፅዳት እቃ 3000 ብር፣ ኤሌክትሮኒክስ 42000 ለመኪና ጎማ 10000 እና ፈርኒቸር 6000 ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይችላሉ።

8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው በመፈራረምና የድርጅቱን ክብ ማህተም በማድረግ ዋናና ኮፒውን በመለየት 2ቱንም ፖስታዎች ማለትም ዋናና ኮፒውን የተጫራቹን ስምና አድራሻ በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ አየር ላይ ከወጣበት ተከታታይ ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን 3፡30 ድረስ ፅ/ቤቱ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በልጋ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:31 ታሽጎ በዛው ቀን ከጠዋቱ ከ4፡00 ሰዓት ይከፈታል። 11ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።

10. ተጫራቹ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች መ/ቤቱ ባዘጋጀው ናሙና መሠረት እቃዎቹን በማየት ዋጋውን ሞልቶ ማቅረብ መቻል አለበት።

11. መ/ቤቱ ጨረታውን እንዳዋጭነቱ በተናጠል ወይም በጥቅል ሊሰጥ ይችላል።

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. አሸናፊ የሆነ ተጫራች በራሱ ወጪ ንብረቱን ቡልጋ ከተማ አስተዳደር ቅጥር ግቢ በማምጣት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለበት።

14. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፁ በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር ይገለፃሉ።

15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011 673 9506 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

አድራሻ፡- ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሃን በሚወስደው መንገድ ከአዲስ አበባ 65 ኪ.ሜ ርቀት ከፍቼ ገነት ከተማ አለፍ ብሎ

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የቡልጋ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-28
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ አየር ላይ ከወጣበት ተከታታይ ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:31 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-28 12:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ አየር ላይ ከወጣበት ተከታታይ ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ ከ4፡00 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Bulga City Administration FEDB
  • Buyer address: አዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሀን በሚወስደው መንገድ ከአዲስ አበባ 65 ኪ.ሜ ርቀት ከፍቼ ከተማ አለፍ ብሎ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 18, 2026)
  • Posted at: 2026-09-18T09:50:10.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders