Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አዲስ አበባ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ አላቂ የጽሕፈትና የፅዳት ዕቃዎች እና መሣሪያዎች፣ የተለያዩ የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች፣ ለቢሮ መሣሪያዎች ጥገና የሚውሉ ዕቃዎች፣ የመረጃ ቴክኖሎጂ መሣሪያዎችና ተዛማጅ ዕቃዎች ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር AA/N01/001/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አዲስ አበባ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ አላቂ የጽሕፈትና የፅዳት ዕቃዎች እና መሣሪያዎች፣ የተለያዩ የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች፣ ለቢሮ መሣሪያዎች ጥገና የሚውሉ ዕቃዎች፣ የመረጃ ቴክኖሎጂ መሣሪያዎችና ተዛማጅ ዕቃዎች ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፣
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፣ ቲን ሰርተፊኬት ያላቸው እና ማስረጃ የሚያቀርቡ፣
3. የዘመኑን ግብር በመክፈል ግዴታቸውን የተወጡና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ፣ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከሰነዳቸው ጋር አያይዘው የሚያቀርቡ፣
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና፤ ለሎት አንድ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ)፣ ለሎት ሁለት ብር 12,000.00 (አስራ ሁለት ሺህ)፣ ለሎት ሦስት ብር 7,000.00 (ሰባት ሺህ)፣ ለሎት አራት ብር 4,000.00 (አራት ሺህ)፤ ለሎት አምስት ብር 8,000.00 (ስምንት ሺህ)፤ ለሎት ስድስት ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ)፤ በሲፒኦ (CPO) ወይም በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አካባቢ አንበሳ ጫማ ፋብሪካ (ዳርማር) ፊትለፊት ዳሽን ባንክ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 102 ላይ በሚገኘው የቅ/ጽ/ቤታችን ግዥና ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒውን ለብቻ በማድረግ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ጋዜጣው ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ቅዳሜን እስከ 6፡00 ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅ/ጽ/ቤቱ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።
7. የጨረታው መክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ሲሆን ይከፈታል።
8. ተጫራቾች ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ቅ/ጽ/ቤቱ ናሙና ላቀረበባቸው ዕቃዎች ናሙናዎቹን በማየት የመጫረቻ ዋጋቸውን መሙላት ይኖርባቸዋል።
9. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ7 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን የዕቃው ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የውል ማስከበሪያ በሲፒኦ (CPO) ወይም በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል በመፈጸም አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች በሙሉ ቅ/ጽ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለበት።
10. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አካባቢ የቀድሞው አንበሳ ጫማ ፋብሪካ (ዳርማር) ፊትለፊት ዳሽን ባንክ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202
ስልክ ቁጥር፡- 011 557-7122 ወይም 011 557-7093
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አዲስ አበባ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-01
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-01 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa No. 1 Medium Tax Payers Office
- Buyer address: ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አካባቢ አንበሳ ጫማ ፋብሪካ (ዳርማር) ፊትለፊት ዳሸን ባንክ ሕንፃ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 19, 2026)
- Posted at: 2026-09-19T07:58:27.000Z
- Source: 2merkato