Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን የጎሮ ጉቱ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2019 በጀት አመት ለመስሪያ ቤታችን ሥራ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያና የጽዳት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ፈርኒቸር፣ የተሽከርካሪ መቀየሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ግልፅ ጨረታ መለያ ቁጥር 1/2019

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን የጎሮ ጉቱ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2019 በጀት አመት ለመስሪያ ቤታችን ሥራ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያና የጽዳት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ፈርኒቸር፣ የተሽከርካሪ መቀየሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት የሥራ መስክ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ኮፒ አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸውና ለሚያወዳድሩባቸው ዕቃዎች ዋጋ ከብር 10,000(አስር ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ ተጫራቾች ለጨረታው ያዘጋጁትን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ለጐሮ ጉቱ ወረዳ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ዋስትና በሲፒኦ 15,000 (አስራ አምስት ሺህ) ብር ማቅረብ አለበት።
  • ተጫራቾች በአንድ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርቶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በግልፅ በማስቀመጥ ሰነዱ ላይ ስምና ፊርማ እንዲሁም የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋና እና ኮፒውን በሁለት የተለያዩ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉን በደብዳቤ ከተገለጸለት በኋላ ለጨረታ ማስከበሪያ ካስያዘው 10% በማስያዝ ወይም የተመረጡትን ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ ካስረከበ በኋላ የጨረታ ማስከበሪያው ይመለስለታል።
  • ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሐሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም።
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ ከወረዳው ፍ/ቤት ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
  • የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 04:00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በምስራቅ ሐረርጌ ፍርድ ቤት በግልፅ ይከፈታል።
  • ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የናሙና ዝግጅት ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ናሙና ማቅረብ አይቻልም፤ ናሙና ያላቀረቡ ተጫራቾች ከውድድር ውጪ ይሆናሉ።
  • ተጫራቾች የሚቀርቧቸው ዕቃዎች በጥራት ደረጃቸው ጥሩ መሆን ያለባቸው ሲሆን ዋስትና ማቅረብ አለባቸው። የማጓጓዣ እና የጭነት ወጪ በተጫራቾች ይሸፈናል።
  • መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የጐሮ ጉቱ ወረዳ ፍርድ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-07
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 04:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-07 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 04:30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የጐሮ ጉቱ ወረዳ ፍርድ ቤት
  • Bid bond: 15,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 19, 2026)
  • Posted at: 2026-09-19T08:16:33.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders