Textile, Garments and Uniforms
በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 አስተዳደር ኒው ኤራ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 አስተዳደር ኒው ኤራ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት በ2019 ዓ/ም በ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን መግዛት ይፈልጋል።
|
የሎት አይነት
|
የCPO መጠን
|
|
ለሎት 1 የደንብ ልብስ እቃዎች |
10,000/አስር ሺህ/ብር
|
|
ለሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች
|
5,000/አምስት ሺህ/ብር
|
|
ለሎት 3 የሕትመት ስራዎች
|
3,000/ሶስት ሺህ/ብር
|
|
ለሎት 4 አላቂ የሕክምና እቃዎች |
3,000/ሶስት ሺህ/ብር
|
|
ለሎት 5 አላቂ የትምህርት እቃዎች
|
5,000/አምስት ሺህ/ብር
|
|
ለሎት 6 አላቂ የጽዳት እቃዎች
|
5,000/አምስት ሺህ/ብር
|
|
ለሎት 7 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
|
5,000/አምስት ሺህ/ብር
|
|
ለሎት 8 የፕላንት ማሸነሪንግ ጥገና |
5,000/አምስት ሺህ/ብር |
|
ለሎት 9 የህንጻ ቁሳቁስና ልዩ ልዩ የጥገና ስራዎች |
5,000/አምስት ሺህ/ብር
|
|
ለሎት 10 ቋሚ እቃዎች
|
10,000/አስር ሺህ/ብር
|
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ አቅራቢ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል።
1.ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
2. የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ።
3. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
4. ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ለእያንዳንዱ ሎት ከላይ በተገለፀው መሰረት ከባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ በት/ቤቱ ስም ማሰራትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6.የጨረታ አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉበት እቃ ዋስትና በካሽ ወይም የውል ማስከበሪያ (BID BOND) 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ኒው ኤራ ነኛና መ/ት/ቤት ፋይናንስና ግ/ን/አስ/ቢሮ ቁ.5 ዘወትር በስራ ስዓት መጥቶ መውሰድ ይኖርበታል።
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን እቃዎች የሚሸጡበትን ዋጋና ሌሎች መረጃዎችንም በሁለት በታሸገ ኢንቨሎፕ ኮፒና ኦርጅናል በማለት እንዲሁም CPOውን ከኦሪጅናሉ ጋር በማያያዝ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት ቆይቶ በ11 ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡በተጨማሪም መስሪያ ቤቱ የጨረታውን 20% መቀነስ ወይም መጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በመ ቤቱ ግ/ፋ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ክፍል ድረስ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 011 126 7510 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ ፡- ፒያሳ ጊዮርጊስ ቤ/ክ አጠገብ ቴሌ ፊትለፊት
በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 አስተዳደር ኒው ኤራ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-02
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት ቆይቶ በ11 ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Bid opening: 2026-10-02 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት ቆይቶ በ11 ቀን ከጠዋቱ 4፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: New Era Elementary and Secondary School
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 20, 2026)
- Posted at: 2026-09-21T08:18:19.000Z
- Source: 2merkato