Stationery

የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ለአምቦ ከተማ አስተዳደር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ደንብ ልብስ፣ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች፣ የመኪና ጎማ፣ ለቴክኒክ ሙያ እና ስልጠና የሚውሉ ዕቃዎች አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 01/2019

የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ለአምቦ ከተማ አስተዳደር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፤ የጽዳት ዕቃዎች፤ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ ደንብ ልብስ፤ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች፤ የመኪና ጎማ፤ ለቴክኒክ ሙያ እና ስልጠና የሚውሉ ዕቃዎች አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ስለምፈልግ መስፈርቶችን የሚያሟሉ አቅራቢ ድርጅቶችን በማወዳደር ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡-

1. ከተጠቀሰው ስራ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው የ2018 የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈለ፤ የግብር ከፍይነት መለያ ቁጥር (Tin Number) ያለዉ፤ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፤ እንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ (supplier list) ሆኖ ከሚመለከተው አካል ማስረጃውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም ከሚያገኘው ገቢ ላይ ታክስ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ።

2. ከሙስና እና መሰል ብልሹ አሠራር ድርጊቶች ነጻ የሆና እና የሀገሪቱን እና የክልሉን ሕግ የሚያከብር።

3. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) በጨረታው ዶክሜንት ላይ የተገለጸው የገንዘብ መጠን በአምቦ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000015202037 ላይ ለየብቻ ብሩን ገቢ በማድረግ ኦርጅናል የገቢ ደረሰኝ (Bank advice) ኦርጅናል ፖስታ ውስጥ አሽገዉ ማቅረብ ይኖርበታል።

4. የጨረታ አሸናፊው ካሸነፈ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋ ላይ የጨረታ ዉል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።

5. በጨረታ ሠነዱ ላይ ስልጣን ባለዉ አካል/የድርጅቱ ባለቤት/ ሥም፤ ፊርማ፤ የድርጅቱን ማህተም፤ የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር በፖስታ ላይ መገለጽ አለበት።

6. ተጫራቾች የጨረታዉን ኦርጅናል ከኮፒዉ ጋር በታሸገ ፖስታ አድርጎ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ 2/2/2019 ዓ.ም በ 8፡00 ሰዓት የጨረታዉ ሳጥን ተዘግቶ በዛዉ ዕለት በ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።

8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በአምቦ ከተማ አስተዳደር ህንጻ 5ኛ ፎቅ መሰብሰብያ አደራሽ ይከፈታል፡፡ ጫረታዉ በሚከፈትበት ቀን ተወዳዳርዎች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸዉ ባለመገኘታቸዉምክንያት ጫረታዉን ከመክፈት አያስቀርም፡፡ ጫረታዉ የምዘጋበት እና የምከፈትበት የአድራሻ ለዉጥ ካለ በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳዉቅ መሆኑን እናገልጻለን።

9. የጨረታዉን ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ ሾርት ኮድ (short code) 518219 ኦብሬተር አይድ (Operator ID) 182149 ላይ በቴለ ብር በመክፈል የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን የምሰጣቸውን ደረሰኝ በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ከአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ከቢሮ ቁጥር 02 መዉሰድ ይችላሉ።

10. አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊ የሆነበትን ዕቃ በደብዳቤ ከተሰጠበት ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ህጋዊ ዉል መፈረም ይኖርበታል።

11. ጨረታዉን ለማደናቀፍ የሚሞክር ከጨረታው ዉጪ እንዲሆን ተደርጎ ለወደፊት በማንኛዉም የመንግስት ግዥ እንዳይሳተፍ ይደረጋል።

12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 011 260 9448/011 236 4462

የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-12
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-10-12 14:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ambo City Administration Finance Office
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 20, 2026)
  • Posted at: 2026-09-21T08:34:44.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders