Textile, Garment and Leather
የካ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የ2019 ዓ.ም. ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Textile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsTextile, Garments and Uniforms
Addis Ababa
More tags
MaterialsEducation and TrainingCleaning and Janitorial Equipment and ServiceOffice Machines and AccessoriesOffice Supplies and ServicesStationeryEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomAmharic2merkatoየካ ቅድመ 1ኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ መለያ ቁጥር የካ/መ 001/2019
የካ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የ2019 ዓ.ም ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1/ የሰራተኛ ደንብ ልብስ
- ሎት 2/ አላቂ የትምህርት እቃዎች
- ሎት 3/ አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 4/ አላቂ የፅዳት እቃዎች
- ሎት 5/ ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
ከላይ ዝርዝራቸው የተጠቀሱትን እቃዎችን ለማቅረብ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ
- የዘመኑ ግብር የከፈለ
- የቫት ከፋይ የሆነ
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይና የቲን ቁጥር የሚያቀርብ
- ህጋዊ ደረሰኝ (ካሽ ሪጂስተር ደረሰኝ) ማቅረብ የምትችሉ
- ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆነ ከጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተፃፈ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ተጫራቾች የግዢ ጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድቦንድ / በየሎቱ የበጀቱ 0.5% ወይም ሎት 1/ ለ ብር 8,000 /ሥምንት ሺህ ብር ብቻ ፤ ሎት 2/ 7,000 /ሰባት ሺህ ብር ብቻ ፤ ሎት 3/ 4,000/ አራት ሺህ ብር ብቻ ፤ ሎት4/ 8,900 /ስምንት ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር ብቻ፤ ሎት 5/ 10,000 /አስር ሺህ ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ማስረጃ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ውል ሲገቡ የውል ማስከበሪያ /ቢድቦንድ 10% በባንክ በተረጋገጠ ማስረጃ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ ኦርጅናልና ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ አስረኛው የስራ ቀን ድረስ ማቅረብ አለባቸው ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም እንዲሁም ከተጠየቀው እስፔሲፊኬሽን ውጪ እቃ ማቅረብ አይፈቀድም።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት መወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማቸውና ፊርማቸውን እና የድርጅታቸው ማህተም አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው።
- በውድድሩ አሸናፊ የሚሆኑ ተወዳዳሪዎች ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ከ8ኛው ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ንብረቱን ት/ቤቱ ድረስ ገቢ ማድረግ አለባቸው።
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በተለምዶ አበቤ ሱቅ ፊት ለፊት ያለውን አስፓልት ተሻግሮ እንግሊዝ ኤንባሲ ጎን ባለው አስፓልት 100 ሜትር ገባ ብሎ
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 668-6087/ 09 11-83-22-42/ 09 32-89-86-96 መጠየቅ ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡- ዋጋው የሚሞላው በወሰዳችሁት የጨረታ ሰነድ ላይ ነው
የካ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-02
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-02 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የካ ቅድመ 1ኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 20, 2026)
- Posted at: 2026-09-21T08:43:57.000Z
- Source: 2merkato