Stationery

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የላፍቶ የመ/ደ/ት/ቤት በ2019 ዓ.ም. በጀት ዓመት ሚያስፈልጉትን ዕቃዎች ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የላፍቶ የመ/ እና መለስተኛ ደረጃ/ት/ቤት የ2019 ዓ.ም

1ኛ ዙር (01/2019)

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የላፍቶ የመ/ደ/ት/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ሚያስፈልጉትን፡-

  • ሎት 01 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
  • ሎት 2 የደንብ ልብስ
  • ሎት 3 አላቂ የጽዳት ዕቃዎች
  • ሎት 04 አላቂ የላብራቶሪ ዕቃዎች
  • ሎት 5 አላቂ የሕክምና ዕቃዎች
  • ሎት 6 ቋሚ ዕቃዎች
  • ሎት 07 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
  • ሎት 08 የተለያዩ የጥገና ዕቃዎች

የላፍቶ የመ/ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት አንደኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ከላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ብቃት ባላቸውና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

  1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቲንና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክሮ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ የአንዱን ሎት የጠቅላላ ዋጋ 2 ፐርሰንት ከጨረታው ሰነዱን ሞልተው ሲመልሱ አብረው ማስገባት የሚችሉ፡-
  3. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በተከታታይ በ10 የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኣንድ ሎት በመክፈል በንፋስ ስልክ ክ/ ከተማ የላፍቶ የመ/ደ/ት ቤት ቢሮ ቁጥር 13 ግዥ ክፍል ቢሮ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማስገባት ማህተም በማድረግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 13 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 10ኛው ቀን በ10፡30 ተዘግቶና ታሽጎ በቀጣዩ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት በት/ቤቱ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 13 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ እሁድና ቅዳሜ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት 01፡02፣03፣04፣05፣07፣08 ድረስ ላሎት ናሙና የዕቃውን መገለጫ/ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለሎት 06 ግን በእስፔስፍኬሽኑ መሰረት ይሆናል።
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ዕቃ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
  8. የዘገየ ጨረታና መከፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው ላፍቶ የመ/ደ/ት ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  10. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያና ጥያቄ ከታች ባለው አድራሻና ስልክ መጠቀም ይቻላል።

አድራሻ፡- ን/ስ ላፍቶ ወ.12 ላፍቶ በላይ ዳገቱን እንደጨረሱ በግራ በኩል ቁጥር 1 ኮንደሚኒየም ጎን ይገኛል።

ስልክ ቁጥር፡- 0913060108/0945310257

ማሳሰቢያ፡- የአነሰተኛና ጥቃቅን ተወዳዳሪዎች መወዳደር የሚችሉት በዘርፉ ባወጡት ንግድ ፈቃድ መሰረት ነው።

የላፍቶ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-01
  • Bid closing time: 16:30
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ 10ኛው ቀን በ10፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-02 10:30
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ10፡30 ሰዓት ተዘግቶና ታሽጎ በቀጣዩ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Lafto Elementary School
  • Bid bond: የአንዱን ሎት የጠቅላላ ዋጋ 2%
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Sep 20, 2026)
  • Posted at: 2026-09-21T08:55:55.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders