Printing and Publishing

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አብርሆት ቤተመፃህፍት በ2019 በጀት ዓመት ላቀዳቸው ስራዎች በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በማወዳደር የህትመት አገልግሎት፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የተለያዩ የቧንቧ እቃዎች እና የኤሌክትሪክ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አብርሆት ቤተመፃህፍት በ2019 በጀት ዓመት ላቀዳቸው ስራዎች በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በማወዳደር የህትመት አገልግሎት የደንብ ልብስ ስፌት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የተለያዩ የቧንቧ እቃዎች እና የኤሌክትሪክ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

ጨረታውን ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

1. ተጫራቾች በዚህ በጨረታ ማስታወቂያ የተጠቀሱትን ግዥ ለማቅረብ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣የንግድ ስራ ፈቃድ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀ፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ የተመሰከረ /CPO/ ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 50,000 ሎት 2 የደንብ ልብስ ስፌት እና የስራ ጫማ 50,000.00 ሎት 3 የተለያዩ የኤሌክትሪክ እቃዎች 50,000.00 ሎት 4 የቧጓቧ እቃዎች 50,000 ሎት 5 የህትመት አገልግሎት 30,000.00 ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500 አምስት መቶ ብር ብቻ/በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000738436893 በመክፈል ከቢሮአችን ከፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር ቢ35 በመቅረብ ሰነዱን መግዛትና ቢሮ ቁጥር ቢ 21 ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፣

4. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ ለብቻ፣ ቴክኒካል ኦርጅናል ኮፒ ለብቻ ብሎ በመለየት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቅዳሜን ጨምሮ ዘወትር ከጧቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በግዥ ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፣

5. ጨረታው በአየር ላይ ከዋለ በ11ኛው ቀን በ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው ቁጥር 810 ይከፈታል። ሆኖም እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፣

6. የጨረታው አሽናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ከ 7 ቀናት በኋላ ይመለሳል፣

7. የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በፅሁፍ በተገለፀ ከ 7/ሰባት/ ቀናት በኋላ እስከ 15 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ ወዲያውኑ ወደ ግዥ ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል መጥቶ ውል መፈረም አለበት። ይህ ባይፈፅም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።

8. አሸናፊው ድርጅት ውል ከፈፀመ በኋላ በውሉ መሰረት በሚሰጠው ትእዛዝ መሰረት ለአገልግሎት ለማቅረብ ምቹ ማድረግ አለበት፣

9. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ መረጃ
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አብርሆት ቤተመፃህፍት
በስልክ ቁጥር 09 23 02 67 36
አድራሻ 4 ኪሎ ፓርላማ ፊት ለፊት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አብርሆት ቤተመፃህፍት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-02
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-02 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Abrahot Library
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 20, 2026)
  • Posted at: 2026-09-21T09:03:04.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders