Equipment and Accessories

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 በካራቆሬ አፀደ ሕፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2019 ዓ.ም የሥራ ዘመን የቢሮ መገልገያዎችና የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 በካራቆሬ አፀደ ሕፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2019 ዓ.ም የሥራ ዘመን የቢሮ መገልገያዎችና የተለያዩ ዕቃዎችን ማለትም፡-

  • ሎት 1 ቋሚ ዕቃ ኤሌከትሮኒክስ (6313)
  • ሎት 2 የደንብ ልብሶች (6211)
  • ሎት 3 የጽሕፈት መሣሪያና ሌሎች (6212)
  • ሎት 4 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች (6215)
  • ሎት 5 የተለያዩ መሣሪያዎችና መጻሕፍት (6219)
  • ሎት 6 ሌሎች አላቂ የፅዳት ዕቃዎች (6218)
  • ሎት 7 የሕክምና ዕቃዎች (6214)
  • ሎት 8 ቋሚ ዕቃዎች (6314)
  • ሎት 9 ሕትመት (6213) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1. የጨረታው ቁጥር 001/2019 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።

2. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር /supplier list/ ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ በባለሥልጣኑ በመንግሥት አካል የተሰጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

4. ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፍኬትእና የታክስ ከፋይነት ቲን ቁጥር ሊኖራቸው ይገባል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት በኮ/ቀ/ ክ/ከ/ ወረዳ 03 በሚገኘው በካራቆሬ አፀደ ሕፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ግራር ባጃጅ መያዣ ከፍ ብሎኮንደሚኒየም አለፍ እንዳሉ ከመስቀሉ ፊት ለፊት ቢሮቁጥር 4 ከ/ሂአስተዳደር ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30_10፡00 ከምሳ ሰዓት ውጪ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

6. በጨረታ ሰነዱ ላይ ያለውን ዕቃ ናሙና (ሳንፕል) ማቅረብ ግዴታ መሆኑን እየገለጽን በአካል ማቅረብ የማይቻል ከሆነ በፎቶ ወይምድርጅቱ ድረስ በመውሰድ ማሳየት ግዴታ አለባቸው።

7. አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ሌላው ተንተርሶ መስጠት አይችልም።

8. ገዥው በኣካል የሚገዛውን ዕቃ እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።

9. ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን (ፋይናንሻል) እና ፎቶ ኮፒውን (ቴክኒካል) ሰነዶችን ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ወይም ቢሮ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓትከ2፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል።

11. የሚቀርበው የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ የድርጅቱ ኃላፊ ስምና ፊርማ የድርጅቱ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር መኖር አለበት።

12. ለአሸናፊ ተጫራቾች በሰነዱ ውስጥ የተመለከተውን ጊዜ ገደብ ማለትም እስከ 7 ቀን ድረስ የቀርበው የውልማስከበሪያ ያሸነፉበትን የዕቃ ዋጋ 10% ገቢ አድርገው ውል መዋዋል አለባቸው።

13. መሥሪያ ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ 6 ወር ድረስ ውሉን ቢያድስም ባያድስም የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. በጨረታ ሰነድ ላይ ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮች ካሉ የማብራሪያ ጥያቄ በጽሑፍ ከጨረታው መክፈቻ 2 ቀን ወይም 3 ቀን በፊት ማቅረብ ይቻላል።

15. ተጫራቾች በጨረታው ሂደት ቅሬታ ካላቸው በት/ቤቱ ከ/ሂ/ግ/ን/አስተዳደር እና ጠ/አዝ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ቅሬታቸውን በጽሑፍ ማቅረብ ይችላሉ። በደጋፊ የሥራ ሂደቱ የማይፈታ ከሆነ ደረጃውን ጠብቀው ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ይችልሉ። ጨረታው ውጤት በተገለፀ በ5ቀን (አምስት) ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ያላቀረበ ተጫራች በውጤቱ እንደተስማማ ተቆጥሮ ግዥው ከአሸናፊው ጋር ውል ይፈጽማል።

16. አሸናፊው ድርጅት የግዢውን ውል ከፈረመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ ዕቃውን ገቢ ማድረግ አለበት።

17.የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክር ማንኛውም ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይሆናል።

18. ማንኛውም ተጫራች ለሚያስገባቸው ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት እንዲሁም ያሸነፉበትን ዕቃዎች ት/ቤቱ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው።

19. የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት

  • ለሎት 1 (11,000ብር)
  • ሎት 2 (35,000ብር)
  • ሎት 3 (20,000ብር)
  • ሎት 4 (30,000ብር)
  • ሎት5 (10,000ብር)
  • ሎት 6 (25,000)
  • ሎት 7 (6,000)
  • ሎት 8 (8,000)
  • ሎት 9 (4,600)

20. ማንኛውም ነጋዴ በሚያመጣው ሳምፕል ላይ ማህተምም ሆነ ስልክ ቁጥር መፃፍ አይቻልም።

21. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው።

  • አድራሻ፡-ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ካራቆሬ ግራር ኮንደሚንየም መስቀሉ ፊትለፊት ከወረዳ 03 ጤና ጣቢያ ወረድ ብሎ ይገኛል።
  • ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡- 011 348-1999
  • ማሳሰቢያ፡- አነስተኛና ጥቃቅን የሆናችሁ ተወዳዳሪዎች የምታመጡት ደብዳቤ የአምራች ድርጅት መሆን አለበት።
  • በተጨማሪ በደብዳቤው ላይ የድርጅቱ ኃላፊ ስምና ፊርማ ሊኖረው ይገባል።

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 በካራቆሬ አፀደ ሕፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-02
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-02 12:00
  • Bid opening (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kara Kore Kindergarten and Primary School
  • Buyer address: ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ካራቆሬ ግራር ኮንዶሚኒየም መስቀሉ ጋ ከወረዳ 03 ጤና ጣቢያ ወረድ ብሎ ይገኛል
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Sep 20, 2026)
  • Posted at: 2026-09-21T09:23:40.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders