Stationery

በግንቦት 20 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2019

በግንቦት 20 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት በ2019 ዓ.ም ከመደበኛ እና ከውስጥ በጀት ደረጃቸውን የጠበቁ ኦርጅናል የሆኑ

  • ሎት1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያ፣
  • ሎት2 የደንብ ልብስ፣
  • ሎት3 የጽዳት እቃዎች ፣
  • ሎት4 የስፖርት ትጥቅና ዕቃዎች ፣
  • ሎት 5 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን እንዲሁም
  • ሎት 6 የቤተ ሙከራና ምርምር እንዲሁም የህክምና እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት ቀጥሎ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታው እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡

  1. ከመንግስት ግዥ ኤጀንሲ ወይም ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ዌብ ሳይት ላይ በዘርፉ የአቅራቢነት ምዝገባ የተመዘገበ፣ህጋዊ የታደሰና ከሚያቀርቡት እቃ ወይም አገልግሎት ጋር ተዛማጅነት ያለው የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ተመዝጋቢ የሆኑና የታክስ ከፋይነት መለያ ቁጥር(Tin No ) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት1 ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር)፣ሎት2 ብር 15,000(አስራ አምስት ሺህ ብር)፣ሎት3 ብር 5,000(አምስት ሺህ ብር) ሎት4 ብር 10,000(አስር ሺህ ብር) ሎት 5 ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) እና ሎት6 በብር 5,000(አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ CPO በት/ቤቱ ስም ተሰርቶ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 200ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
  4. የጨረታ ሳጥኑን በ10ኛው የስራ ቀን 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከት/ቤቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት መፈጸም ይኖርባቸዋል፡፡
  6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡-የት/ቤቱ አድራሻ ሳሪስ ከዳማ ሆቴል ወደ ሀና በሚወስደው አስፓልት ኮኮብ

ፓስታና ዱቄት ፋብሪካ ከፍ ብሎ ከአስፋልት 200 ሜትር ገባ ብሎ ነው፡፡

ስ.ቁ 011-419-80-66/011-419-1505

በግንቦት 20 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-01
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የስራ ቀን 11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-02 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ginbot 20 Secondary and Preparatory School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Sep 20, 2026)
  • Posted at: 2026-09-21T10:07:19.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders