Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የካ አባዶ ጤና ጣቢያ የሚያስፈልጉትን እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ 01/2016 ዓ.ም
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የካ አባዶ ጤና ጣቢያ የሚያስፈልጉትን
- ሎት 1 (1) የሠራተኞች ደንብ ልብስ የጨረታ ማስከበሪያ 2000፡
- ሎት 1 (2) የሰራተኞች ደንብ ልብስ ስፌት ጨረታ ማስከበሪያ 2000፣
- ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 2000
- ሎት 3 ልዩ ልዩ ህትመቶች የጨረታ ማስከበሪያ 2000 ፤
- ሎት 4 የፅዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 2000
- ሎት 5 የመገልገያ መሳሪያዎች የጨረታ ማስከበሪያ 2000
- ፤ ሎት 6 (1) በህንፃና በቁሳቁስ ላይ የሚገጠሙ የጥገና እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 3000፤
- ሎት 6 (2) የአልሙኒየም የሴራሚክ እና የሸማች ሱቅ ስራ የጨረታ ማስከበሪያ 3000 ፤
- ሎት 7 (1) የህክምና ቋሚ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 3000፤
- ሎት 7 (2) አላቂ የህክምና እቃ
- ሎት 8 በቢሮ ውስጥ የሚገጣጠሙ ቋሚ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 3000፤
- ሎት 9 የጭነት መኪና አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ 2000፤ በ2019 የበጀት ዓመት ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
በዚህ ጨረታ ላይ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች -
በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል
የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ፕሪንት አውት /ኮፒ/ ማቅረብ የሚችል
ለህክምና ዕቃዎች ለሚወዳደሩበት ዘርፍ ከኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት የተሰጠ ፈቃድ፣
የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት /TIN / ያላቸው
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር በየሎቱ ማቅረብ ሲኖርባቸዉ ደምሮ ሲፒኦ ማስገባት አይቻልም። በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /በጥሬ ገንዘብ / እንዲሁም አሸናፊ ከሆኑ የጠቅላላ ዋጋ 10% ሲፒኦ የውል ማስከበሪያ ማቅረብ አለባችሁ። ዘግይቶ የመጣ ፖስታ ተቀባይነት የለውም።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ (ለየሎት) የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከጤና ጣቢያው ቢሮ ቁጥር 403 መውሰድ ይችላሉ።
ሳንፕል የሚያቀርቡ ተጫራቾች አሸንፈው በሚገቡ ጊዜ በዋጋ ልዩነት በሚል ሰበብ አይነት እና ይዘታቸው የተለወጠ እቃ ማቅረብ አይችሉም።
ተጫራቾች አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ የተደረገ ፋይናንሽያል እና ቴክኒካል ዶክመንት ዋጋ ማቅረቢያዉ ላይ የድርጅቱ ማህተም ተመቶ በተለያየ በታሸገ ፖስታ በማሸግ ለአስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ከረዳት ፋይናንስ ቢሮ በመግዛትና በመውሰድ በጨረታ ሰነዱ ላይ የምትወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን ያካተተ ዋጋ ነገር ግን (የአልሙኒየም፣ ሴራሚክ እና የሸማች ሱቅ ስራ) ከቫት ውጭ በማድረግ ሞልታችሁ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን በጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጐ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀናት የሚከፈት ይሆናል።
እቃ ሲያስገቡ ከ11፡00 ሰዓት በፊት ማስገባት አለበት። ክፍያ የሚፈፀመው እቃውን ጤና ጣቢያ አምጥታችሁ በባለሙያ ተፈትሾ ማሟላት የሚገባውን ሁሉ አሟልቶ ሲገኝ መሆኑን እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ፡- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ
በስልክ ቁጥር 011 893-1217
የካ አባዶ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-10-02
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-02 12:00
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Yeka Abado Health Post
- Buyer address: ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ስሙ የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም ግቢ ውስጥ G-7 ብሎክ 306 ጀርባ አካባቢ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Sep 20, 2026)
- Posted at: 2026-09-21T11:08:20.000Z
- Source: 2merkato