Finishig Works
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ መካኒሳ ዋናዉ መስሪያ ቤት የሞላሰስ ማከማቻ ታንከር ኢፖክሲ የዉስጥ ሽፋን ሥራ የሚሰራ ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ቁጥር 002/2019 ዓ.ም
ድርጅታችን መካኒሳ ዋናዉ መስሪያ ቤት የሞላሰስ ማከማቻ ታንከር ኢፖክሲ የዉስጥ ሽፋን ሥራ የሚሰራ ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
1. የታደሰ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
2. የማይመለስ ቫትን አካቶ በብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሠነዱን መካኒሳ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ገንዘብ ቤት በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
3. ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኰፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የሚቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑ በግልጽ መቀመጥ አለበት፤
4. ለጨረታ ዋስትና የሚሆን የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% በሲፒኦ ለብቻው በኢንቨሎፕ በማሸግ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፤
5. ተጫራቾች የሚያስገቧቸውን ሠነዶች ጥቅምት 5 ቀን 2ዐ19 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡ዐዐ ሠዓት መካኒሳ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ግዥ ቢሮ 5ኛ ፎቅ ቁጥር 503 ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡15 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
6. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ
ፖ.ሣ.ቁ. 3516
ፋክስ 011 551 3299
Addis Ababa
Ethiopia
Tender details
- Deadline: 2026-10-15
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-10-15 10:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: National Alcohol and Liquor Factory (NALF)
- Buyer address: Addis Ababa, Ethiopia
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 /አምስት መቶ ብር/
- Published on: Qelal Tenders (Sep 21, 2026)
- Posted at: 2026-09-21T11:15:47.000Z
- Buyer website: https://www.nalf.com.et
- Source: Qelal Tenders