Equipment and Accessories
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የመብራት እቃዎችን እና የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsBuilding and Finishing Materials
Addis Ababa
Description
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በግዥ መለያ ቁጥር 003/2019 ለተቋማችን የስራ አገልግሎት የሚውሉ የመብራትና የመብራት እቃዎችን እና የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
|
ተ/ቁ |
የግዥ ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
ሎት 1 |
የመብራትና የመብራት እቃዎች |
50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) |
|
ሎት 2 |
የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎች |
50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) |
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ/የቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችሉ፣
- የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው እና የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር/Tin No /ያላቸው
- ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ በመ/ቤታችን ስም የተዘጋጀ CPO ወይም የተረጋገጠ የባንክ ጋራንቲ በተቀመጠው ሎት መሰረት ማስያዝ አለባቸው። ነገር ግን CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ በተቀመጠዉ ሎት መሰረት ያላስያዘ ተጨራች ከጨረታ ውጪ ይሆናል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የሚችሉት በሪፖርተር ጋዜጣ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10(አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ብቻ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች ከተራ ቁጥር1 እስከ ተራ ቁጥር 6 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተጫራቾች በሚወዳደሩበት በእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300(ሦስት መቶ) በድርጅቱ ስም በተከፈት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000493811049 በመክፈል ያስገቡበትን ዲፖዚት ስሊፕ ይዘዉ በመምጣት ዘውትር በስራ ሰዓት ቃሊቲ ማስልጠኛ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት መግዛት ይችላሉ።
- አሸናፊው ድርጅት ጥራቱን የጠበቀ ዕቃ ካላቀረበ በራሱ ወጪ የመለወጥ ግዴታ አለበት፣
- መ/ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይቻልም፤ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ፡-
- 9.1 ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒው ለየብቻ፣
- 9.2 ፋይናንሽያል ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ፣
- 9.3 ሲፒኦን በሌላ ፖስታ ለብቻው አሽገው የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በማድረግ ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
- ተጫራቾች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በትክክል መሙላት አለባቸው፣
- ከጥቃቅንና አንስተኛ ለሚመጡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በነጻ ለመዉሰድ፡-
- ሀ. ከደራጃቸው መ/ቤት ሕጋዊ ደብዳቤ ማምጣት ይኖርባቸዋል፣
- ለ. በመመሪያ መሰረት ለምወዳደሩበት ዕቃ አምራች መሆን ይኖርባቸዋል
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ ወይም አገልግሎት ዝርዝር ላይ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል። እንዲሁም አሸናፋው የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት በመ/ቤታችን ቀርቦ ውል መዋዋል አለበት ይህ ባይሆን ግን ለዋስትና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለመንግሰት ገቢ ይሆናል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በሚገኝው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ሰኞ መስከረም 25/2019 ዓ/ም እስከ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከተጠቀሰው ሰዓት ዘግይቶ የመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ጨረታው የሚከፈተው ሰኞ መስከረም 25/2019 ዓ/ም ጠዋት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አስተዳደር ሕንፃ ስር በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት
ስልክ ቁጥር 011 470 8116
መስከረም 10/2019
Tender details
- Deadline: 2026-10-05
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-10-05 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa Light Rail Transport Service Enterprise (AALRTSE)
- Buyer address: Addis Ababa Light Rail Transit Service(Kality Depot) 1st Floor
- Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Reporter (Sep 20, 2026)
- Posted at: 2026-09-21T13:19:43.000Z
- Source: Qelal Tenders