House and Building Sale

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን እና በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼  (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
  • ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀን እና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
  • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከከም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
  • ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
  • በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሽናፊ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
  • የጨረታ ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 7፣ ለገህር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አማ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የፎርክሎዠር እና ዴት ሊቲጌሽን ዲቪዥን የጨረታ ክፍል ውስጥ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 515 1153 እና 011 515 0711 ኢአ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
  • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተ.ቁ

የተበዳሪው ስም

የመያዣ ሰጪው ስም

የንብረቱ ዓይነት እና ኣገልግሎት

የቦታው ስፋት በካ.ሜ

የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር

የጨረታው የሚካሄድበት ቀን

የምዝገባ ሰዓት

የጨረታ ሰዓት

1

ድሪም ቲም ትሬዲንግ ኃ/ የተ/የግ/ማህበር

የ፻ አለቃ ትርፌ መኮንን ደጀኔ

G+2 የሆነ የመኖሪያ ቤት

 

175

ሊዝ/ዕጣ/8756/95

 

በቀድሞ አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 28 (በአሁኑ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ)

15,661,250.21

 

ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም.

4:30-5:30

5:30-6:00

 

2

አቶ ታደለ ደምሰው አግዘው

 

አቶ መስፍን አግዘው በላይነህ

G+6+T የሆነ የንግድ ህንፃ

328

190118/112/2007

ኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን፣ አሰላ ከተማ፣ ቀበሌ 04

50,128,922 96

ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም

4:30-5:30

5:30-6:00

 

3

ተበዳሪው

G+4 የሆነ የንግድ ህንፃ

355

18980/71/2006

ኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን፣ አስላ ከተማ፣ ቀበሌ 04

27,872,978.83

 

ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም

8:30-9:30

9:30-10:00

 

 


Tender details

  • Deadline: 2026-10-23
  • Bid closing time: 16:00
  • Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-10-23 16:00
  • Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
  • Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Reporter (Sep 20, 2026)
  • Posted at: 2026-09-21T14:06:07.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders