House and Building Sale

አሐዱ ባንክ አ.ማ. መኖሪያ ቤት (G+1) በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ማስታወቂያ

ቁጥር - 27/2018

አሐዱ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 (እንደተሻሻለው) በተሰጠው ስልጣን እና ውክልና መሠረት ቀጥሎ የቀረቡትን ንብረቶች በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የተበዳሪው ስም

የመያዣ ሰጪ ስም

አበዳሪ  ቅርንጫፍ

ለሐራጅ የቀረበው ንብረት ዝርዝር መግለጫ

የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር

የሐራጁ የሚከናወንበት

ሐራጁ የወጣው

የንብረቱ አይነት

አድራሻ

የካርታ ቁጥር

የቦታ ስፋት

ቀን

ሰዓት

1

ታጅር ግሩፕ ኢንደስትሪያል ኃየተግ/ማህበር

 

ወ/ሮ ሀምዳ ኡመር አደን

መስቀል አደባባይ

 

መኖሪያ ቤት (G+1)

ሶማሌ ክልል፣ ጅግጅጋ ከተማ፤ ገረብአሴ ክ/ ከተማ፣ ቀበሌ 03 የጎግል ካርታ ኮርድኔት ቁጥር 9,34676,42.82836

37467/18

 

500 ካሜ

 

29,832,750.00

 

ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም

 

ከጠዋቱ 5፡00-6:00

ለመጀመሪያ ጊዜ

የሐራጅ ደንቦች፡-

  1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በአሐዱ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
  2. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ መክፈል አለበት። ካልተከፈለ የተያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል። በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃሉ። በጨረታው ተሸናፊ ለሆኑት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል።
  3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸው ብቻ ናቸው። ተበዳሪ እና ወኪሎቻቸው ባይገኙም ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
  4. የጨረታ አሸናፊ ለሆነው ተጫራች በባንኩ የብድር ፖሊሲ፤ መመሪያ እና ቅደመ ሁኔታ መሠረት ብድር ሊመቻች ይችላል።
  5. የተጫራቾች ምዝገባ ከእያንዳንዱ የንብረት ሐራጅ መዝጊያ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል። በሐራጁ የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም።
  6. የሐራጁ አሸናፊ ገዢ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፤ ከስም ማዛወሪያ ክፍያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ የግብር ግዴታዎችን ገዥው አሸናፊው ይከፍላል።
  7. ተጫራቾች የጨረታው ቀን ከመድረሱ 5 (አምስት) ቀን በፊት ከባንኩ ጋር በመነጋገር በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ በቦታው በመገኘት ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች መጎበኘት ይቻላል።
  8. ተጫራቹ የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በፅሑፍ ሲደርሰው ነው።
  9. ጨረታው የሚከናወነው ጅግጅጋ ከተማ በሚገኘው የአሐዱ ባንክ ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ነው።
  10. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 526 0223 (ሕግ አገልግሎት መምሪያ) ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

አሐዱ ባንክ አ.ማ.


Tender details

  • Deadline: 2026-10-20
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-10-20 12:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ahadu Bank S.C.
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Reporter (Sep 20, 2026)
  • Posted at: 2026-09-21T14:13:55.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders