Cleaning and Janitorial Equipment and Service

ግሎባል ባንክ ኢትዮየጵያ አ.ማ. የጽዳትና ተላላኪ ሥራ የሰው ሃይል አቅራቢ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለተለያዩ ቅርንጫፍ ቢሮዎቹ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጽዳትና ተላላኪ ሥራ የሰው ሃይል አቅርቦት ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 05/2026/27

ግሎባል ባንክ ኢትዮየጵያ አ.ማ የጽዳትና ተላላኪ ሥራ የሰው ሃይል አቅራቢ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለተለያዩ ቅርንጫፍ ቢሮዎቹ ማሰራት ይፈል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን የጨረታ መመሪያ እና መመዘኛዎች የሚያሟላ ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች መወዳደር ይችላል።

1. ተጫራቾች ከሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ስራና አሰሪን ለማገናኘት የተሰጠ ሥራ ፈቃድ ያለውና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ።

2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈለበትን የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ተ.እ.ታ ሰርተፊኬት፣ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት እና ታክስ ክሊራንስ ሰርተፊኬ ማቅረብ የሚችሉ።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ. ስታዲየም ቅርንጫፍ በመክፈል እና የገቢ ደረሰኝ ይዘው በመቅረብ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ራስ አበበ ዳምጠው ጎዳና (ስታዲየም ከኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ) ናሽናል ቢዝነስ ሴንተር ሕንጻ 7ኛ ፎቅ ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ በመቅረብ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 እስከ 11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. የጨረታው ዋጋ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ይሆናል። ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዋጋዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተቱ ሆነዉ ማንኛውንም ወጪና የመንግስት ቀረጥ የተከፈለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል።

6. ግልጽ ጨረታው መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ጠዋት 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባንኩ ዋና መ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል።

7. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- ግሎባል ባንክ ዋና መ/ቤት፣ ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ፣
ስልክ ቁጥር 011 558 1204 ወይም 011 531 8097
ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።


Tender details

  • Deadline: 2026-10-05
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-05 10:15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Global Bank Ethiopia S.C.
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Reporter (Sep 20, 2026)
  • Posted at: 2026-09-21T15:10:11.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders