Business, Industry and Factory Foreclosure

ዳሽን ባንክ አ.ማ. የንግድ ቤት ባለበት ሁኔታ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

የሐራጅ ቁጥር ዳባ/039/26

ዳሽን ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/11 በተሰጠው ስልጣን መሠረት የሚከተሉትን ተበዳሪ ወይም አስያዥ ንብረት ባለበት ሁኔታ በሐራጅ ይሸጣል።

ተ.ቁ

የተበዳሪው ስም

አበዳሪው ቅርንጫፍ

የአስያዥ ስም

ለጨረታው የቀረበው ንብረትና የቦታው ስፋት

የጨረታ መነሻ ዋጋ (ብር)

የጨረታው የሚካሄደበት

ለጨረታው የቀረበው ንብረት

ከተማ፣ ወረዳ፤ ቀበሌ

የካርታ ቁጥር

የቦታ ስፋት

 

ቀን እና ቦታ

 

ሰዓት

 

1

አቶ ጌቴ ይጅቡ አላፌ

ወረታ ቅርንጫፍ

አቶ ጌቴ ይጅቡ አላፌ

የንግድ ቤት

 

ወረታ ከተማ፤ ቀበሌ 01

1826/2013

1250 ካ.ሜ  

29,086,507

 

ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም በባህር ዳር ቀጠና ጽ/ቤት

4:00_

6:00

 

ማሳሰቢያ

1. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (C.P.O) በዳሽን ባንክ አማ ስም በማሰራት በጨረታው ዕለት ይዘው በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ።

2. ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት በባህር ዳር ቀጠና ጽ/ቤት ይካሄዳል።

3. የሐራጁ አሸናፊ /ገዢ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈለው ግብር ታክስ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) እና ሌላ ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ወጪዎችን ገዢው/አሸናፊው/ ይከፍላል።

4. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑን ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል። ባይከፍል ግን ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስለትም:: በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል። በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያሲያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

5. በጨረታው ላይ አስያዥና ተበዳሪ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ፤ ባይገኙ ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል።

6. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሠዓት 10 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል።

7. ጨረታው ተጀምሮ በተቀመጠው ሰዓት ውስጥ ካልተጠንቀቀ ሊራዘም ይችላል።

8. ተጫራቹ የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ ከባንኩ በፅሑፍ ሲደርስው ብቻ ነው።

9. ባንኩ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ አሸናፊ/ ባንኩ በከፊል ብድር ሊያመቻች ይችላል። ባንኩ ብድሩን በማናቸውም ሁኔታ ለአሸናፊው ባይፈቅድ/ባይሰጥ አሸናፊው በዚህ የሀራጅ ደንብ የተቀመጡ ግዴታቸውን አያስቀርላቸውም።

11. ጥቅምት 06 ቀን 2019 ዓ.ም ከ3፡00-3፡30 ሰዓት ዳሸን ባንክ ባህር ዳር ቀጠና ጽ/ቤት በመገኘት በእለቱ ከባንኩ ተወካዮች ጋር በመሆን የሚጫረተዉን የንግድ ቤት መጎብኘት ይችላሉ። 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-320 97-81 ወይም 011-1-70 40-38 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ዳሽን ባንክ አ.ማ.


Tender details

  • Deadline: 2026-10-20
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-20 10:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Dashen Bank S.C.
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Reporter (Sep 20, 2026)
  • Posted at: 2026-09-21T15:30:03.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders