House and Building Foreclosure
የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ ባለሙበት ራሔል አለማየሁ እና የፍ ባለዕዳ እነ ሰለሞን ብሩ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/164150 26/09/2017ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/171271 በ03/04/2018 ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/171271 በ24/03/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር ML/B-14/SN/004 ይዞታው ቤቱ E-ካርታ የሆነ ቤቶ በአቶሰለሞን ብሩ አየለ ስም የተመዘገበ የቤቱ ህንጻ ቁጥር 14 የወለል ቁጥር ግራውንድ (Ground) የሆነ የቤቱ ስፋት 45.63ካ/ሜ የጋራ መጠቀሚያ ስፋት 42.08ካ/ሜ ጠቅላላ ስፋት 87 ካ/ሜ የሆነ የቤቱ አገልግሎት የንግድ የሆነ ንግድ ቤቱ ላይ ቀሪ ያልተከፈለ ዕዳ ወለድን ጨምሮ 50% ያልተከፈለ ዕዳ 1,184,388.50(አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሰማንያ አራት ሺህ ሶስት መቶ ሰማንያ ስምንት ከ50/00) ያለበት ሲሆን ቤቱ በአሁኑ ሰዓት ካርታ ያልወጣለት ምክንያቱም 1ኛ የፍ/ባለዕዳ እና 2ኛ ተጠባባቂ የነበሩት ግለሰብ መካከል ባለው ዕግድ ምክንያት ነው በማለት የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ገልፆልናል፡፡ ስለዚህ የተባለው እግድ የተነሳ ስለሆነ የጨረታ አሸነፊ ለወደፊት ካርታ ሂደት ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን መሃደሩ የሚደራጅለት ይሆናል። የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 3,824,557 (ሶስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሃያ አራት ሽህ አምስት መቶ ሃምሳ ሰባት) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆነ ታውቆ መስከረም 8 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምከንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.171272 በቀን ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በድጋሚ ሐራጅ ጨረታ ሆኖ 1/4ኛ ብር 956,139.25 (ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስድስት ሺህ አንድ መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ከ25/100) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ታህሳስ 2 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.PO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/ አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-12-11
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-12-11 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Nov 07, 2026)
- Posted at: 2026-11-07T08:31:35.000Z
- Source: Qelal Tenders