Machinery and Equipment
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ንብረቶች በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለብድር ገንዘብ ማካካሻነት በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የመያዣ ንብረቶች በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው/ የመያዣ ሰጪው ስም |
የንብረት አድራሻ
|
የንብረት ዝርዝር |
የቦታ ስፋት (በሄክታር |
የጨረታ መነሻ ዋጋ (በብር) |
የጨረታ ሁኔታ
|
የጨረታ ደረጃ |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ማጃንግ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግል ማህበር |
ጋምቤላ ህ/ብ/ክ/መ፤ ማጃንግ ዞን፣ መንገሺ ወረዳ፣ አሽኔና ባያ ቀበሌ |
የመስኖ እርሻ እና ግንባታዎች፣ የእርሻ ማሽነሪዎች፤ ተሽከርካሪዎች 99.33 ሄክታር ላይ የተተከለ የሙዝ ቋሚ ተክል ያለው |
1000 ሄክታር
|
393,239,016.73
|
ድርድር
|
የመጀመሪያ
|
ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡00- 6፡00 ሰዓት
|
|
2 |
ኤም ዋይ ሹዝ ኤንድ አማራ ብሔራዊ ክልላዊ ሌዜር ማኑፋቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማ |
አማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ደብረ ብርሃን ከተማ 09 ቀበሌ
|
የጫማ እና የቆዳ ማምረቻ ፋብሪካ(ለትግበራ ላይ ያለ) የህንፃ ግንባታዎች፤ ማሽነሪዎች እና የኤልክትሪክ ሥራዎች |
6.83 ሄክታር
|
457,236,714.80
|
ዝግ
|
ሁለተኛ
|
ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡00- 6፡00 ሰዓት
|
ማሳሰቢያ፤
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በፎርማቱ ላይ በመጥቀስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ሁለተኛ ታወር ምድር ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሣጥን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ ከሦስተኛው ቀን ጀምሮ ከማጃንግ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግል ማህበር የተረከበውን ንብረት ለመግዛት እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ከኤም ዋይ ሹዝ ኤንድ ሌዜር ማኑፋቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተረከበውን ንብረት ለመግዛት እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡50 ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
3. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል:።
4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዡ በተመለከተው ቀንና ሰዓት በባንኩ ዋናው መ/ቤት ይካሄዳል። ህጋዊ ሰውነት ያለው አካላት ወኪል በጨረታው ለመሳተፍ የሚቀርብ ሰው የማህበሩን መመስረቻ ፅሁፍ/መተዳደሪያ ደንብ ከእነማሻሻዎቹ ካሉ፤ የንግድ ምዝገባ፣የንግድ ፈቃድ፣ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን እና የተረጋገጠ የውክልና ስልጣን ሰነዶችን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
5. 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰነ ክፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል።
6. አንዳንድ የድርጅቱ ንብረቶች የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆኑ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል።
7. የማጃንግ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግል ማህበር የስራ እንቅስቃሴ ያልተቋረጠ በመሆኑ አሸናፊው ከግዢው ዋጋ በተጨማሪ ያልተሰበሰበ ወይም በክምችት ላይ ያለ የሙዝ ምርት በርክክብ ወቅት በሚደረስበት የትመና ዋጋ መሰረት በጥሬ ገንዘብ መግዛት ይችላል፣
8. የንብረቱ ስመ ንብረት ለገዥው እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል። ገዥው ጉዳዩን ተከታትሎ ያስፈፅማል።
9. ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው ከተቻለ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ሲሆን አሸናፊው በባንኩ ብድር ፖሊሲና የአሰራር ስርዓት መሰረት አስፈላጊውን የብድር መስፈርቶች ካሟላና ፕሮጀክቱን የሚያስቀጥል ከሆነ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል።
10. የጨረታ አሸናፊው ማጃንግ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግል ማህበር ቋሚ ሰራተኞች በሙሉ ከመብትና ጥቅማቸው ጋር መረከብ ይጠበቅበታል።
11. በጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው።
12. በጨረታው ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦንጎይንግ ኮንሰርን ፕሮጀክትስ እና አኳየርድ አሴትስ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-524-5373 /011-524-4269 ደውሎ ማግኘት ይቻላል። የመያዣ ንብረቶቹን መጐብኘት የሚፈልግ ከዳይሬክቶሬቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል።
13. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
Tender details
- Deadline: 2026-10-27
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታው ቀን ይለያያል
- Bid opening: 2026-10-27 12:00
- Bid opening (note): የጨረታው ቀን ይለያያል
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Reporter (Sep 20, 2026)
- Posted at: 2026-09-21T15:42:07.000Z
- Source: 2merkato