Textile, Garments and Uniforms

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 የደጅአዝማች በላይ ዘለቀ ቁ.2 ቅ/አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም. ልዩ ልዩ የትምህርት ግብዓቶችን እና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ በመደበኛ በጀት እና በውስጥ ገቢ በጀት አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል

Description

የመጀመሪያ ዙር የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር/001/2019 ዓ.ም

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 የደጅአዝማች በላይ ዘለቀ ቁ.2 ቅ/አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም ልዩ ልዩ የትምህርት ግብዓቶችን እና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ በመደበኛ በጀት እና በውስጥ ገቢ በጀት አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ 

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የጨረታ ማስከበሪያ CPO

ሎት-1 የደንብ ልብስ ብር 5000፣ ሎት-2 የደንብ ልብስ ስፌት ብር 1000፣ ሎት-3 የፅዳት እቃዎች ብር 5000፣ ሎት 4 የህትመት ስራዎች ብር 1000፣ ሎት 5 አላቂ የህክምና እቃዎች ብር 500፣ ሎት-6 አላቂ የትምህርት እቃዎች ብር 2500፣ ሎት-7 እስቴሽነሪ /የፅህፈት መሣሪያዎች ብር 4000፣ ሎት-8 አጋዥ መፅሐፍት ብር 500፣ ሎት-9 የኤሌትሪክ፣ የኤሌክትሮኒክስ እና የተለያዩ የቧንቧ እቃዎች ብር 2000፣ ሎት-10 ቋሚ እቃዎች ብር 3200፣ ሎት-11 የጥገና ስራዎችን ብር 3000፣ ሎት 12 የትራንስፖርት አገልግሎት ብር 500 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት በባንክ የተረጋገጠ CPO ማሲያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በቻች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

1. አግባብነት ያለው ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡

2. የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡ ከፋይናንስ ሚ/ር በአቅራቢነት ሊስት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. የጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች በሚወዳደሩበት እቃ ልዩ አስተያየት እንዲደረግለት ከፈለገ የአምራችነት ወይም እሴት የጨመረበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

4. የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከቢሮ ቁ.5 መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ10ኛው ቀን 11፡30 ተዘግቶ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቾቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል ፡፡

6. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ መግለጫ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል አና ኮፒ በማድረግ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁ.3 ማስገባት አለባቸው ::

7. ተጫራቾቾ መጫረት የሚችሉት በንግድ ፍቃድ ዘርፍ ብቻ መሆን አለበት፡፡ 

8. ተጫራቾች በእያንዳንዱ እቃ ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቅድሚያ ያላቀረቡ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጪ ይሆናሉ።

9. አሸናፊው በአሸነፈባቸው እቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

10. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

11. በማስታወቂያው ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

12. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

13. በዚህ ጨረታ ላይ ከተጠቀሱት እቃዎች ብዛት ት/ቤቱ ከውል በፊት 20% መጨመር ወይም 20 % መቀነስ ይችላል፡፡
አድራሻ፡- አዲሱ ገበያ ከፍ ብሎ ፂዮን ሆቴል ጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ ::

ለበለጠ መረጃ: ስልክ ቁጥር 0111270985 / 0111547428 እና 0111547484 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ ::
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 የደጅአዝማች በላይ ዘለቀ ቁ.2 ቅ/አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-01
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 11፡30
  • Bid opening: 2026-10-02 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Dej Azmach Belay Zeleke No.2 Elementary School
  • Buyer address: አዲሱ ገበያ ከፍ ብሎ ፂዮን ሆቴል ጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 21, 2026)
  • Posted at: 2026-09-22T06:47:04.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders