House and Building Sale

አዋሽ ባንክ አ.ማ. ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

አዋሽ ባንክ አ.ማ ከታች በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: በመሆኑም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከታች የቀረቡትን መመሪያዎች በመገንዘብ በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

  1. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በየትኛውም የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ ሒሳብ ቁጥር 01540000544500 በተጫራቹ ስም ገቢ በማድረግ ደረሰኙን አዲስ አበባ ከተማ ልደታ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው አዋሽ ባንክ ባልቻ ሳፎ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ሕንፃና የተወረሱ ንብረቶች አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 1-08 በማቅረብ ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  2. የጨረታው መነሻ ዋጋዎች እና ሌሎች መረጃዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች የሚወዳደርበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4ኛ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲፒኦ (CPO) በአዋሽ ባንክ አክስዮን ማህበር ስም በማሰራትና በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኘውን ቅፅ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ አዋሽ ባንክ ዋናው መ/ቤት 12ኛ ፎቅ የግዥ እና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት አዋሽ ባንክ ዋናው መ/ቤት 12ኛ ፎቅ የግዥ እና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ውስጥ የሚከፈት ይሆናል።
  4. ከጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት በኋላ፣ እንዲሁም ያለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
  5. የጨረታው አሸናፊዎች ንብረቶቹን ያሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)፣ የስም ዝውውር እና ተያያዥ የመንግስት ወጪዎችን የመክፈል ግዴታ አለባቸው።
  6. የጨረታው አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ15(አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ አጠቃለው በመክፈል ንብረቱን መረከብ ይኖርባቸዋል:: በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውሰጥ ክፍያውን ፈፅመው ንብረቱን ካልተረከቡ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
  7. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

.

የንብረቱ መግለጫ

የንብረቱ ዓይነት

የቦታ ስፋት

ምርመራ

1

ሸገር ከተማ፣ ቡራዩ /ከተማ፣ ለኩ ከታ ወረዳ፣ በተለምዶ በግ ተራ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ የሚገኝ መጋዘን

መጋዘን

 

594.46 .

 

-

2

ሸገር ከተማ፣ ቡራዩ /ከተማ፣ ለኩ ከታ ወረዳ፣ በተለምዶ ስማቸው መጋዘን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኝ መጋዘን

መጋዘን

 

937.89 .

 

-

3

አቃቂ ቃሊቲ /ከተማ፣ ወረዳ 09 ቂሊንጦ ሳይት ብሎክ 202 ላይ የሚገኝ የንግድ ኮንዶሚንየም ቤት

የንግድ ኮንዶሚንየም ቤት

57.38 .

 

ሁለቱ ቤቶች በአንድ ላይ ተዋህደው ለጨረታቀርበዋል::

 

4

አቃቂ ቃሊቲ /ከተማ፣ ወረዳ 09 ቂሊንጦ ሳይት ብሎክ 202 ላይ የሚገኝ የንግድ ኮንዶሚንየም ቤት

የንግድ ኮንዶሚንየም ቤት

48.50 .

 

5

ሽገር ከተማ፣ ኮዬ ፈጬ /ከተማ፣ ቱሉ ዲምቱ ሳይት፣ የሕንፃ ቁጥር 01 ላይ የሚገኝ የንግድ ኮንዶሚንየም ቤት

የንግድ ኮንዶሚንየም ቤት

95.65 .

 

-

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 530-31-02/04 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።


Tender details

  • Deadline: 2026-10-08
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-08 10:15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Awash Bank Share Company
  • Bid bond: 25%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Reporter (Sep 20, 2026)
  • Posted at: 2026-09-22T07:14:22.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders