Stationery
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2019
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር የ2019 ዓመት የ1ኛ ዙር ግዥ አላቂ የፅህፈት መሳሪያ፣ ዕቃ እና የደንብ ልብስ፣ የጽዳት ዕቃ የትራንስፖርት ፒካፕ አይሱዚ ሀይገር መስተንግዶ የወንበር ጠረጴዛ ጥገና የፎቶ ኮፒ ኮምፒተር ፐሪንተር አክሰሰሪ ጥገና የመድረክ ዲኮር የዘር የጉልበት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
1. የዘመኑ ግብር የከፈሉ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ በዘርፉ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል እንዲሁም ቫት ወይም ቲኦቲ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
2. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት1(አላቂ የጽሕፈት መሣሪያ) ብር 13812 ሎት3 (የደንብልብስ) ብር13512 ሎት2 (የጽዳትዕቃ) ብር 18865 ሎት4(ፕሪንተር ፍሪጅ ካሜራ)20000 ሎት5(ህትመት) 6742 ሎት6 (መስተንግዶ) 2000 ሎት7(ዘር) 1000 ሎት 8(ትራንስፖርት) 2000 ሎት9 (ጠረቤዛ ወንበር ጥገና) 2800 ሎት 10(ፎቶ ኮፒ ፕሪንተር ኮምፒዩተር ጥገና) 1800 ሎት11(የመድርክ ዲኮር3350 በማስያዝ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3. የተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለተሸናፊው ደርጅት ወዲያውኑ ተመላሽ ሲሆን አሸናፊው ድርጅት ደግሞ የውል ማስከበሪያ የውሉን 10% አስይዘው እንደተፈራረሙ በጨረታው ለጨረታ ማስያዣነት የተያዘው ብር ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
4. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘው ሰነድ ለያንዳንዱ ሰነድ በማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ (አስር) የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት ምድር ላይ ቢሮ ቁጥር 1 የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን አድራሻቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡እንዲሁም ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለያንዳንዱ ካቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
6. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት 10ኛው ቀን ከሰዓት 11፡30 ላይ ታሽጎ በማግስቱ 4፡00 (አራት ሰዓት) ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ ስራ ሂደት ሂደት ቢሮቁጥር I ላይ ይከፈታል።
7. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
8. በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ ልዩ ድጋፍ የሚደረግላቸው ተወዳዳሪዎች ለሚያቀርቡት ምርት(ዕቃ) ተጨማሪ እሴት ለሚጨምሩ ወይም ለሚያመርቱ ምርት ብቻ ይሆናል፡፡ ይህንንም ድጋፍ ደብዳቤ ሲያመጡ አምራች /እሴት ተጨማሪ መሆናቸው በአደራጃቸው ወረዳ በጽ/ቤቱ ሀላፊ የተፈረመ መሆን አለበት ይህ ካልሆነ ከጨረታው ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ይደረጋሉ።
- ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥሮች ደውለው ይጠይቁ አድራሻ ጎፋ ገብርኤል 100 ሜትር ገባ ብሎ ፀሀይ ፔንሲዮን አጠገብ ሶፊያ ሞል ገባ ብሎ
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በሚያስገቡበት ወቅት የዕቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ያቀረቡት ናሙናም በ6 ወር ውስጥ ካልወሰዱት ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
በ/ን/ስ/ላ/ክ/ከ/የወ06 ፋ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-01
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት 10ኛው ቀን ከሰዓት 11፡30
- Bid opening: 2026-10-02 10:00
- Bid opening (note): በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት 10ኛው ቀን ከሰዓት 11፡30 ላይ ታሽጎ በማግስቱ 4፡00 (አራት ሰዓት)
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: ለያንዳንዱ ሰነድ 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 21, 2026)
- Posted at: 2026-09-22T07:14:37.000Z
- Source: 2merkato