Equipment and Accessories

አዲሲቷ ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/መ/የገንዘብ የቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር ዘመናዊ የኮር ባንኪንግ ሲስተም (CBS) ለማቅረብ፣ ለመጫን፣ ለማበጀት (Customization)፣ ስልጠና ለመስጠት እና የጥገና አገልግሎት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

ድርጅት፡ አዲሲቷ ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/መ/የገንዘብ የቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር

የፕሮጀክት ስም፡ የኮር ባንኪንግ ሲስተም (Core Banking Solution) ግዥና ትግበራ

የማጣቀሻ ቁጥር፡ AECBS 001

የወጣበት ቀን፡ መስከረም 04 ቀን 2019 ዓ.ም. / Sep 14, 2026

አጠቃላይ መግለጫ

አዲሲቷ ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/መ/የገንዘብ የቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር ዘመናዊ የኮር ባንኪንግ ሲስተም (CBS) ለማቅረብ፣ ለመጫን፣ ለማበጀት (Customization)፣ ስልጠና ለመስጠት እና የጥገና አገልግሎት ለማቅረብ ብቁና ተፈላጊውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች የታሸጉ የጨረታ ሰነዶችን እንዲያቀርቡ ይጋብዛል።

የሥራ ወሰን

ተመራጩ አቅራቢ የሚያቀርበው ጠንካራ የሶፍትዌር ሲስተም የሚከተሉትን የሥራ ክፍሎች ማካተት አለበት፦

  • የአባላት ምዝገባ እና የአክሲዮን/የአባልነት አስተዳደር
  • የቁጠባና ተቀማጭ ሂሳብ አስተዳደር
  • የብድር ማመልከቻ፣ ሂደት፣ ክትትል እና ግምገማ
  • የጠቅላላ ሂሳብ መዝገብ (General ledger) እና የፋይናንስ ሪፖርት
  • የመተሳሰሪያ ቻናሎች (ሞባይል ባንኪንግ፣ All ወይም USSD)
  • የሲስተም ደህንነት፣ በሚና ላይ የተመሠረተ የመጠቀሚያ ፈቃድ እና የመረጃ ማስተላለፍ (Data Migration)
  • የተሳትፎ መስፈርቶች
  • ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የሚከተሉትን ህጋዊና ቴክኒካዊ ሰነዶች ማቅረብ አለባቸው፦
  • ትክክለኛና ተቀባይነት ያለው የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት
  • የግብር ክሊራንስ ማስረጃ
  • በፋይናንስ ተቋማት በተለየ በቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበራት (SACCOs)
  • የኮር ባንኪንግ ሲስተም በመተግበር የተረጋገጠ ልምድ ያለው
  • ከሶፍትዌሩ ዋና አምራች (OEM) የተሰጠ የተፈቀደ ወኪልነት ወይም የአጋርነት ሰርተፊኬት (እንደ አግባብነቱ)

የጨረታ ዝርዝር ሁኔታ

  • የጨረታ ሰነድ መግዣ/መውሰጃ፡ ሙሉ የጨረታ ሰነዱን ከቢሮአችን ሾላ ገበያ፣ ለምለሚ መርካቶ ህንፃ፣ 4ኛ ፎቅ ማግኘት ይቻላል።
  • የጨረታ ሰነድ ዋጋ፡ 1,000 (አንድ ሺህ) ብር፣ በCBE ሂሳብ ቁጥር 1000218597975 በአዲሲቷ ኢትዮጵያ የቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር ስም የሚከፈል።
  • የጨረታ ማቅረቢያ የመጨረሻ ቀን፡ Sep 30, 2026 ከቀኑ 9፡00 ሰዓት (03:00 PM)። ዘግይተው የሚቀርቡ ጨረታዎች ተቀባይነት አያገኙም።
  • ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

የመገኛ መረጃ

አድራሻ፡

ሾላ ገበያ፣ ለምለሚ መርካቶ ህንፃ፣ 4ኛ ፎቅ

የካ ክፍለ ከተማ

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 94 40 40 61/51 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አዲስቷ ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/መሰ/የቁ/ብ/የህ/ስራ ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-10-10
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid opening: 2026-10-10 15:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: አዲሲቷ ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/መ/የገንዘብ የቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር
  • Bid bond: 1,000 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 21, 2026)
  • Posted at: 2026-09-22T07:59:42.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders