Equipment and Accessories

ለኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የተለያዩ የቢሮና የስልጠና ግብዓቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ 

ለኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት በ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ማውጣት ስለፈለገ የሚከተሉትን የቢሮና የስልጠና ግብዓቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1 ቋሚ የቢሮ ዕቃ  5,000
ሎት 2- አላቂ የቢሮ ዕቃ  5,000
ሎት 3 -የፅዳት እቃዎች 5,000
ሎት 4 የሆቴል ዲፓርትመንት ዕቃዎች  5,000
ሎት 5 የአይሲቲ እቃዎች  5,000
ሎት 6 የኮንስትራክሽን እቃዎች 5,000
ሎት 7 የጋርመንት እቃዎች  5,000
ሎት 8 የአግሮ እቃዎች  5,000
ሎት 9 የማኑፋክቸሪንግ እና ፈርኒቸር እቃዎች  5,000
ሎት 10 የእስፖርት ዕቃዎች  5,000
ሎት 11 ህትመት  5,000
ሎት 12 የመኪና እቃዎች  5,000
ሎት 14 የመኪና ኪራይ  5,000
ሎት 15 የመኪና ጥገና  5,000
ሎት 16 የሚወገዱና የሚጠገኑ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች  5,000
  1. በሎት 8 ላይ የወተት ላም መኖ፤ ሳር፤ የአተር ገለባ ለአንድ አመት የሚቆይ ሆኖ በየ3ወሩ የሚታደስ ይሆናል።
  2. ተጫራቾች በአቅራቢነት በመንግስት ኤጀንሲ የተመዘገቡ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የመኪና ጥገና ለአንድ አመት የሚቆይ
  4. ህትመት ለአንድ አመት የሚቆይ ሆኖ በየ6 ወሩ የሚታደስ
  5. የሆቴል አላቂ እቃዎች ለአንድ አመት ሆኖ በየ3 ወሩ የሚታደስ
  6. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑ የንግድ ግብር ከፋይ ፈቃድን ያደሰና ማስረጃው ግልጽ የሆነና የሚነበብ ኮፒ ማቅረብ የሚችል ።
  7. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆኖቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል መሆን አለባቸው።
  8. የጨረታ ሰነድ በድርጅቱ ስም ያልገዛ ተወዳዳሪ በጨረታ መሳተፍ አይችልም።
  9. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን በየሎቱ የማይመለስ 500.00 / አምስት መቶ/ ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲ-ፒ -ዮ ብቻ በየሎቱ አሰርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  11. ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ 10/አስር/ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰአት ላይ ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል ።
  12. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸው ኮሌጁ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ ቫትን ያካተተ ጠ/ዋጋ የሚለውን በግልጽ ሞልተው ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህን በግልጽ ሞልተው ያላቀረቡ ተጫራቾች ዋጋዉ ቫትን ያካተተ ነው ተብሎ ይወሰዳል።
  13. ተጫራቾች በሰነዱ ላይ እንደተጠቀሰው ቴክኒካል ዶክመንት ወይም ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  14. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ዋናውንና ኮፒውንበተናጠል በታሽገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።ተጫራቾች በራሳቸው ትራንስፓርትና አውራጅ የጉልበት ሰራተኛ በመመደብ ለኮሌጅ ንብረት ግምጃ ቤት ያስረክባሉ።
  15.  ኮሌጅ የተሸለ አማራጭ ካአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 369 7215

አድራሻ አዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ከዘነበወርቅ ወደ

ወይራ ሰፈር በሚወስደው መንገድ 250 ሜትር ወደ ግራ ገባ ብሎ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ስራ ና ክህሎት ቢሮ

ኮልፌ ኢንዱስትሪል ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-02
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ 10/አስር/ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰአት
  • Bid opening: 2026-10-02 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ 10/አስር/ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰአት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kolfe Industrial College
  • Buyer TIN: 0050529376
  • Buyer address: አዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከዘነበወርቅ ወደ ወይራ ሰፈር በሚወስደው መንገድ 250 ሜትር ወደ ግራ ገባ ብሎ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር በየሎት
  • Published on: Addis Zemen (Sep 21, 2026)
  • Posted at: 2026-09-22T08:20:04.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders