Personal Care Products and Services
በአዲስ አበባ ከተማ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለሥልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት ከነማ ፋርማሲ የኮስሞቲክስ እና ወተት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 003/2019
በአዲስ አበባ ከተማ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለሥልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ እና በዙሪያዋ ለሚገኙ ነዋሪዎች ለሁሉም ከከተሞች ጤና መድህን ተጠቃሚዎች ለፌዴራል ጤና መድህን ተጠቃሚዎች መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ጥራታቸውና ፈዋሽነታቸው የተረጋገጡ መድኃኒቶች እና የህከምና መገልገያዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ በ53 መድኃኒት ቤቶች እና የጅምላ ንግድ አከፋፋይ ድርጅቶች የዱቤ /credit እና የጥሬ ገንዘብ/ cash ሽያጭ አገልግሎት እየሰጠ ያለ የመንግስት የልማት ድርጅት ነው።
ስለሆነም ድርጅቱ ከነማ ፋርማሲ የኮስሞቲክስ እና ወተት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል መስፈርቱን የምታሟሉና ብቁ የሆናችሁ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- በንግድ ዘርፍ ወይም በመስኩ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው እና የቲን ማስረጃዎች።
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት (ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ ) ጉለሌ ክ/ከተማ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS / ኤስ ኤም ኤስ ኤስ / ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን 4፡30 ሰዓት የጨረታው ሳጥን የሚታሸግ ስለሆነ አርፍዶ የሚመጣ ተቀባይነት የለውም፡፡ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን በድርጅቱ ግዥ ዳይሬክቶሬት ክፍል 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 የሚከፈት ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከፒያሳ ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS / ኤስ ኤም ኤስ ኤስ / ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403፤
የሥራ ሰዓት፡- ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ፤ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0118-27-91-23
በአዲስ አበባ ከተማ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለሥልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-10-02
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-02 10:30
- Bid opening (note): ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Kenema Pharmacy Enterprise
- Buyer address: ከፒያሳ ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS (ኤስ ኤም ኤስ ኤስ) ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 21, 2026)
- Posted at: 2026-09-22T08:36:32.000Z
- Source: Qelal Tenders