Stationery

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የቀበና ጤና ጣቢያ የፋይናንስና ግዥ በጨረታ ቁጥር ቀ/ጤ/ጣቢያ 1/2019 በጀት ዓመት ለጤና ጣቢያው እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ግዥ መለያ ቁጥር የቀ/ጤ/ጣ01/2019 ዓ.ም.

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የቀበና ጤና ጣቢያ የፋይናንስና ግዥ በጨረታ ቁጥር ቀ/ጤ/ጣቢያ 1/2019 በጀት ዓመት ለጤና ጣቢያው እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 አላቂ የቢሮ የጽሕፈት መሣሪያዎች
  • ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት 3 የደንብ ልብስ እና ስፌት
  • ሎት 4 የተለያዩ የጥገና እቃዎች
  • ሎት 5 ቋሚ እቃዎች እና ኮምፒውተር ተዛማች እቃዎች
  • ሎት 6 ህትመት
  • ሉት 7 ኮምፒውተር ተዛማች እቃዎች ጥገና
  • ሎት 8 ፍሳሽ ቆሻሻ ማንሳት የኮምፒውተርና ተዛማች ዕቃዎች ጥገና
  • ሎት 9 መድኃኒቶች፣ የላብራቶሪ ሪኤጀንት፣ አላቂ የሕክምና ዕቃዎች ቋሚ የሕክምና ዕቃ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው ቫት ተመዝጋቢ የሆነ የዘመኑን ግብር የከፈለበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡና የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና ቲን ነምበር ያላቸው።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቀበና ጤና ጣቢያ ፋይናንስ ክፍል ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት እቃ 8,000.00 /ስምንት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. ማንኛውም ተጫራቾች ሰነዱን ለማስገባት በሚመጡበት ጊዜ ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ሳምፕል አብሮ ማስገባት አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን ከሲፒኦ ጋር በአንድ ፖስታ ኮፒ ሰነድ በሌላ ፖስታ አሽገው የድርጅቱን ማህተም በማድረግና በፊርማ በማረጋገጥ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6፡00 ሰዓት እንዲሁም 7፡30-11፡00 ሰዓት ድረስ የጤና ጣቢያው የግ/ን/አስ/ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታው ሳጥን በ11ኛ የሥራ ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአራዳ ክ/ከተማ በቀበና ጤና ጣቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የአንዱ ዋጋም ሆነ ጠቅላላ ዋጋ ሲቀመጥ ቫት አካቶ መሆን አለበት።
  7. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራቾች በተመዘገቡበት ንግድ ፍቃድ ዘርፍ ብቻ መወዳደር አለባቸው።
  8. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ ውል ከተፈራረመበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀን ውስጥ እስከ ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ ይኖርበታል።
  9. የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ኦርጅናልና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  10. ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡ ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ፡- አድራሻ ቀበና ሼል የኦሮሚያ ደን ሕንፃ ገባ ብሎ ቀበና መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን አጠገብ ነው።

ስልክ ቁጥር፡-011-8-11 21 55 / 0111 23 56 07 ደውስው መጠየቅ ይችላሉ

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የቀበና ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-02
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-02 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ የሥራ ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Arada Sub City Kebena Health Care Office
  • Buyer address: ቀበና ሼል ከመድረሱ በፊት የኦሮሚያ ድን ህንፃ ገባ ብሎ ቀበና ምሥራቅ ፀሐይ መድሃኒያዓለም ቤተክርስቲያን አጠገብ
  • Bid bond: 8,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 21, 2026)
  • Posted at: 2026-09-22T08:41:11.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders