Others

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የዱራሜ ዲስትሪክት ጽ/ቤት መኪና መከራየት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የዱራሜ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገነባቸው የመንገድ ግንባታና ጥገና ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውል የሰርቪስ አይሱዙ፣ የሠራተኞች ማመላለሻ ሰርቪስ ሚኒባስ ሃይሩፍ ወይም  ሀይሱዙ ቅጥቅጥ መኪና የሚያቀርቡ በጨረታ አፈጻጸም መመሪያ ላይ በዝርዝር በተገለፀው መሠረት ከሕጋዊ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ አከራዮች በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፣

በዚሁ መሠረት 

1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምዝገባ ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀትና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ ዋና እና ኮፒ <<ኦርጂናል>> እና <<ኮፒ>> በማያያዝ እና የጨረታ ማስከበሪያውን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በተለያየ ፖስታ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከዲስትሪክቱ የፋይናንስና ሎጅስቲክ ማስተባበሪያ ደጋፊ የሥራ ሂደት መግዛት ይችላሉ፡፡

4 የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከተው መሥፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም ተጫራች ከፍት ነው፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ በዱራሜ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ   ዘ፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኝት የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡

6. ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋ 1% የጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል :: አሽናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 10% የማስያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡

7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው:: ከጨረታ ደንብና መመሪያ ውጪ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡

8. አሸናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ እስከ አምስተኛው ቀን ድረስ ውል ማስከበሪያ አስይዞ ውል መግባት ይኖርበታል፡፡ በተሰጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ውል የማይገባ ከሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡

9. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::  መረጃ፣ ስልክ ቁጥር 0911973776/0926545089

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የዱራሜ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ዱራሜ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-08
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛው ቀን ከቀኑ ዘ፡30 ድረስ
  • Bid opening: 2026-10-09 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Ethiopian Roads Authority
  • Buyer address: Ras Abebe Aregay Street, Engineering Procurement Directorate, Team-3 Ethiopian Roads Authority 1st floor, Room No. 106
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 22, 2026)
  • Posted at: 2026-09-22T08:42:21.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders