Stationery
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ላሎ ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን ለመግዛት እና ለማስጠገን ይፈልጋል
More tags
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር 01/2019
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ላሎ ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ላሉ አገልግሎት ሰጭ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ፡-
- ሎት1፣የፅህፈት መሳሪያ፣
- ሎት2፡- የፅዳት እቃ፤
- ሎት3 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- ሎት4፡-ኮንስትራክሽን ማቴሪያል፣
- ሎት 5 ስፖርት ማቴሪያል ፤
- ሎት 6፡ ፈርኒቸር እና
- ሎት 7፣ ጎማ እና ከነመዳሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስጠገን ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት፡-
1. በዘርፉ የተሰማራና በሙያው የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ነምበር/ ያላቸው
3 የግዥው መጠን ከብር 200,000 እና በላይ ከሆነ የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. የሚገዙ እቃዎችን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የእቃውን ዋጋ በቁርጥ ለሎት1፦ 60,000 ብር፣ ለሎት2 -10,000 ብር ፣ለሎት3፡-20,000 ብር ፣ለሎት4፡- 10.000 ብር፣ ለሎት5፡- 6,000 ብር፣ ለሎት6፡- 5,000 ብር እና ለሎት7 - 10.000 ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
7. ተጫራቾች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት የእቃ ዓይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይቻልም
8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ግዴታ አለባቸው
9. በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋ።
10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አንድ ወጥ በሆነ አንድ ኦርጅናል በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ ንብ/አስ/ቡ/ ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ11 ተከታታይ ቀናት እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ።
11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በመንዝ ላሎ ምድር ወረዳ በግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ውስጥ በይፋ ይከፈታል። ባይገኙም ከመከፈት እይታገድም።
12. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል።
13 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ሎት በማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከመንዝ ላሎ ምድር ወረዳ ገንዘብ ዕ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይችላሉ።
14. ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት በራሳቸው ወጭ ወረዳው ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው።
15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ነው ብሎ ካሰበ በሎት የወጣውን ጨረታ በነጠላ ዋጋ ሊያወዳድር ይችላል
16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የመንዝ ላሎ ምድር ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-02
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ11 ተከታታይ ቀናት እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-02 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Menze Lalo Meder Woreda FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: በእያንዳንዱ ሎት 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 22, 2026)
- Posted at: 2026-09-22T08:58:29.000Z
- Source: 2merkato