Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በሲዳማ ክልል የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ209 በጀት ዓመት ለወረዳው ሴክተር መ/ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የእስቴሽነሪ እና የፅዳት ዕቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በሲዳማ ክልል የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ209 በጀት ዓመት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የእስቴሽነር እና የፅዳት ዕቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት ተጫራቾች ማሟላት የሚያስፈልጋቸው ተግባራት

1. በዘርፉ የንግድ ፍቃድ ያላቸዉ በ2019 ዓ.ም ፍቃዳቸውን ያሳድሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ

2. ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ

3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸዉ

4. በዕቃው አቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

5. የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርበዉ ጠቅላላ ዋጋ ግዥ 20,000 (ሃያ ሺህ) ብር ብቻ፤ የኢትዮጵያ ብር በባንክ የተረጋገጠ ክፍያ CPO በሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ ለገቢዎች ባለ ስልጣን ቅ/ ጽ/ቤት በመቅረብ ከፈሎ የተከፈለበትን ደረሰኝ በማቅረብ የጨረታ ሰነድ ከሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስ/የሥራ ሂደት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።

7. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልተዉ በሰም የታሸገ ኤንቬሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት በሁሉም ዶክመንት ላይ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8. የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት በ16ኛው ቀን በዕለቱ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።

9. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ ሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት።

10. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያቀረበዉን ዕቃ ጥራቱን ያልጠበቀ ከሆነ ዕቃ የተገዛበትን ገንዘብ የመመለስና ወይንም ዕቃ የመለወጥ ግዴታ አለበት።

11. አሰሪ መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

12. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ይከፈታል።

13. የወቅቱን ዋጋ ያላገናዘበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-06
  • Bid closing time: 12:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-06 14:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ16ኛው ቀን በዕለቱ 8፡00 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Sidama Zone Hawassa Surrounding Woreda F/E/D/B
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 21, 2026)
  • Posted at: 2026-09-22T09:10:59.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders