Wood and Wood Working
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የዕንጨት ውጤቶች እና የእንጨት ማሽን ተዛማጅ እቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ፌ.ቤ.ክ ብማጨ/ዕቃ/10/01/2019
1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የዕንጨት ውጤቶች እና የእንጨት ማሽን ተዛማጅ እቃዎች ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/ዕግ/10/01/2019 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
2. ለኮርፖሬሽኑ አገልግሎት የሚያገለግል የዕንጨት ውጤቶች እና የእንጨት ማሽን ተዛማጅ እቃዎች ግዥ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ቴክኒካል ሰነዳቸውንና ዋጋቸውን በተለያዩ በታሸጉ ኤንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው።
|
ተ.ቁ |
የዕቃ ዝርዝር |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
የዕንጨት ውጤቶች እና የእንጨት ማሽን ተዛማጅ እቃዎች ግዥ |
50,000.00 |
3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ በፌዴራል መንግስት ባለቤትነት የተያዙ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የግዥ አፈፃፀም መመሪያ 1070/2017 ሲሆን ከሚፈለገው የዕንጨት ውጤቶች እና የእንጨት ማሽን ተዛማጅ እቃዎች ግዥ ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል።
4. የተሟላ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀረ በሚገኘው ኮርፓሬሽኑ ዋና መ/ቤት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ወይም መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ በባንክ በተመሰከረለት የባንክ ዋስትና ወይም ሲ.ፒ.አ በፌዴራል ቤቶች ኮፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተደደር ዳይሬከተር 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
6. የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር 011-855-3617 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ዌብሳይትWebsite WWW.agh.gov.et
የፖ.ሣ.ቁ. P.O. Box 299
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-10-07
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-10-07 10:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Housing Corporation
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 22, 2026)
- Posted at: 2026-09-22T10:16:23.000Z
- Buyer website: https://www.fhc.gov.et
- Source: Qelal Tenders