Stationery
ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ጥቅል ወረቀት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የሀገር ውስጥ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ቦንድ 80 ግራም 61X86 እና ቦንድ 60 ግራም 61X86 ወረቀት በሪም መልክ እና ባንክ 45 ግራም 82/84 ሴ.ሜ ጥቅል ወረቀት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ሰርተፊኬት እና ሌሎችም የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች በቅድሚያ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ቢሮ ቁጥር 101 በመክፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከሁለተኛው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ድረስ ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ቢሮአችን መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የዋጋቸውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዶችን በአንድ ላይ በፖስታ አሽገው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከግዥ ክፍል በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ፡፡
5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 15 ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማህበሩ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
6. ድርጅቱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡-
ስልክ ቁጥር ........01115 15 50 05/0115 51 88 72
ፋክስ ..................0115 51 86 96
ፖስ ቁጥር.........2365
ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
አዲስ አበባ
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-10-06
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 15 ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-06 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 15 ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Bole Printing P.L.C.
- Buyer address: ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 22, 2026)
- Posted at: 2026-09-22T11:00:23.000Z
- Source: Qelal Tenders