Textile, Garments and Uniforms

በጉለሌ ክ/ከ በወረዳ 8 አስተዳደር ስር የሚገኘው የብርሃነ-ህሊና ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ/ቁጥር 001/2019

በጉለሌ ክ/ከ በወረዳ 8 አስተዳደር ስር የሚገኘው የብርሃነ-ህሊና ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ እቃዎችን አወዳድሮ ከዚህ በታች ባለው ሎት መሰረት መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1፡- ደንብ ልብስ እና የስፌት
  • ሎት 2፡- የእስቴሽነሪ ዕቃዎች እና አላቂ የት/ት ዕቃዎች
  • ሎት 3፡- የፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት 4 - ቋሚ ዕቃዎች

በመሆኑም ከዚህ ቤት የተገለጹትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ ንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነና ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የንግድ ቁጥር (Tin Number) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ጨረታዉን ለመሳተፍ በቅድሚያ የማይመለስ ብር 300(ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ የተቋሙ ግዥ ክፍል በመምጣት መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

4. ጨረታውን መወዳደር የምትችሉ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ እሴት የሚጨምሩ አምራች ሆነው ከአደራጃቸው ተቋም የሚጽፍላቸው ደብዳቤ መሰረት ያለ ክፍያ መጫረት ይችላሉ።

5. አንዱ በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።

6. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 - 15000.00፣ ለሎት 2፡ 10000.00፣ ለሎት 3፡ - 12500.00፣ ለሎት 4፡- 15000.00 ዋስትና ቢያንስ ለስድስት ወር ፀንቶ የሚቆይ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ እስከ የጨረታ መዝጊያ ቀን ድረስ ከዋና ሰነድ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ።

7. ተወዳዳሪዎች ለሚያቀርቧቸው ለእያንዳንዱ ዕቃዎች ከጨረታው መክፈቻ ቀን በፊት ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

8. ጨረታው አሸናፊ ድርጅት ውል ከመፈረማቸው በፊት የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

9. ድርጅቱ በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተጠቀሱትን ዕቃዎች ካለዉ በጀትና የተሻለ አማራጭ ካገኘ ከውል በፊት የዕቃዎቹን 20% የመጨመር፣ የመቀነስ፣ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ተጫራቾች ሰነዱን በመሙላት ኦርጅናሉንና ኮፒውን በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እስከ 10ኛዉ ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ በጉለሌ ክ/ከተማ በወረዳ 8 አስተዳደር ስር የሚገኘዉ ብርሀነ-ህሊና ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

11. ጨረታው በ10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ11ኛዉ ቀን በ3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል ውስጥ ይከፈታል።

12. ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃዎች መሥሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ የማድረስ ግዴታ አለባቸው።

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ከአዲሱ ገበያ ወደ ቶታል በሚወስደው -መንገድ ጎጃም በር አደባባይ ሳይደርሱ መርሐቤቴ ሆቴል አጠገብ ወደ ሩፋኤል በሚወስደው አስፋልት መንገድ ትንሽ ገባ እንዳለ ያገኙታል።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011 154 6225 / 011 127 0755 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የብርሃነ-ህሊና ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ
እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-02
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-03 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ ቀን በ3፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Birehane Hilina Elementary School
  • Buyer address: ጉለሌ ክ/ከ ወ8 ከአዲሱ ገበያ ወደ ቶታል በሚወስደው መንገድ መርሀቤቴ ሆቴል አጠገብ ወደ ሩፋኤል በሚወስደው አስፓልት መንገድ 300 ሜትር ገባ ብሎ ብርሀነ ህሊና ት/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300(ሶስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 22, 2026)
  • Posted at: 2026-09-22T11:09:25.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders