Tri Wheeler, Motorcycles and Bicycles Purchase
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኡራ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ደንብ ልብስ፣ ሞተር ሳይክል፣ ሸራተን ወንበር፣ የመኪና ጎማ፣ ዱንኳን እና ጀኔሬተር በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኡራ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ደንብ ልብስ፣ ሞተር ሳይክል፣ ሸራተን ወንበር፣ የመኪና ጎማ፣ ዱንኳን፣ ጀኔሬተር በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ለመግዛት የሚከተሉትን መስፈረቶች በጨረታ ሠነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የተጫራቾችን መመሪያ የሚያሟሉ ድርጅቶችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
1. በዘርፍ የተሰማሩበት የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው
2. የዘመኑ ግብር የከፈለ
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው
5. የጨረታውን ሠነድ በ.................
6. ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋት 2፡30 እስከ 11፡30 ሠዓት ድረስ በአካል ቀረበው መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የተጫረቱበትን የጨረታ ማስከበሪያ በምድብ የተለያየ ሲሆን በዚህ መሠረት ደንብ ልብስ፤ 50,000 ሺህ ሞተር ሳይክል፤ 50,000 ሺ ሸራተን ወንበር፤ 30,000 ሺ የመኪና ጎማ፤ 30,000 ሺህ ዱንኳን፤ 20,000 ሺህ ብር/በባንክ በተረጋገጠ cpo ከዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 500.00/አምስት መቶ ብር/ በመክፍል መግዛት አለባቸው።
9. የገዙትን የጨረታ ሠነድ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ 5 ቀን ቦኃላ ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
1ዐ. ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጅምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሠዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ27/1/2019 ዓ.ም ይከፈታል ዕለቱ የእረፍት ቀን አሊያም የበዓል ቀን ላይ ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
11. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ ንብረቶቹን የሚያሰረክቡበት ቦታ በቤ/ገ/ክ/መ/ ኡራ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ንብረት ክፍለ ድረስ በማምጠት ይሆናል።
12. ተጫራቾች ዋናው/ኦርጅናል/ማስረጃ በተጨማሪ 2 /ሁለት/ ኮፒ በተለያዩ ፖስታዎች የታሸጉ በድምሩ 3/ ሶስት በማድረግ እንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ማስገባት ይኖርበታል።
13. ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊ ሊሆኑ የሚችለው በነጠላም ሆነ በ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተወዳዳሪ የጨረታው አሸናፊ ሊያደረግ ይችላል።
14. ዋጋ ማቅረብ የምትችሉት በገዛችሁት ሰነድ ብቻ ይሆናል ሙሉ የጨረታ ሰነዱ ማህተም ተመትቶ አብሮ መመለስ አለበት።
15. ማሳሰቢያ፡- ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት ናሙናው ኮሚቴው በድርጅቱ ሄዶ ማየት አለበት።
16.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
17. ተጫራቾች በጨረታው ሠነዱ ላይ የተጠቀሱትን የተጫራቾች መመሪያ ማሟላት ይኖርባቸዋል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-35 04-33 53 ደውሎ ሰነድ መወስድ ይችላሉ
አጭር መግለጫ
የቤ/ጉ/ከ/መ/ የኡራ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2019 ዓ/ም የበጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱና ለኡራ ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሞተር ሳይክል አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ለተጫራቾች የተዘጋጀ መደበኛ የጨረታ ሰነድ ነው።
የተጫራቾች መመሪያ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የኡራ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለመ/ቤቱና ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ደንብ ልብስ፤ ሞተር ሳይክል፤ ሸራተን ወንበር፤ የመኪና ጎማ፤ ዱንኳን፤ ጀኔሬተር ለመግዛት ለተጫራቾች የተዘጋጀው የጨረታ መመሪያ ይሆናል።
1. በዘርፍ የተሰማሩበት የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው
2. የዘመኑ ግብር የከፈለ
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው
5. ተጫራቾች በጨረታ መጫረቻ ሠነዳቸው ላይ የድርጅታቸውን ስምና አድራሻ ስልጣን በተሰጠው የድርጅቱ ኃላፊ ፊርማቸውንና ህጋዊ ማህተማቸውን በማስፈርና የዋጋ ማቅረቢያውን ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የኡራ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በማለት መላክ ይኖርባቸዋል።
6. ድርጅቶቹን ለመመዝገብ በጽ/ቤቱ ሥልጣን የተሰጠው አካል የኡራ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ሲሆን ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር መግልጫ መመሪያ በደንብ በማንበብ ዋጋ ሲሞሉ ከሚደርሰው ስህተት ይድናሉ።ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ባቀረቡት ዋጋ መንተራስ አይችሉም፡፡ አቅረቦ ቢገኝ ከውድድር ውጭ ይደረጋል። የሚሰጡት ዋጋ በጨረታው የሚያቀርቡት የግዥ ዓይነት መለኪያ፤ በነጠላ ዋጋ ከሁሉም ተወዳዳሪዎች ያቀረበ እና ሌሎች በቴክኒክ መግለጫ ላይ የተገለጹትን መስፈርቶች በግልጽ ቋንቋ መፃፉና ድርጅትዎን በመወከል ስልጣን በተሰጠው አካል መፈረሙን እና ማህተም ማረፉን ካረጋገጠ በኃላ መሆን ይኖረበታል።
7. ተጫራቾች በዝርዝር በተፃፉት የግዥ ዓይነቶች በሙሉ ወይም በከፍል መወዳደር ይችላሉ
8. ከዋናው ኦርጅናል/ማስረጃ ዶክመንት በተጨማሪ የሚፈለጉ የኮፒዎች ብዛት 2 ሲሆን ማለትም 1/አንድ/ ኦርጅናል 2/ሁለት፤ ኮፒዎች በድምሩ 3/ሶስት/ በተለያየ በፖስታ የታሸጉ የዋጋ ማቅረቢያ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ እንዲኖረው አይፈቀድም፡፡ በእርሳስ የተሞላ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።
9. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ ቦኃላ ያቀረበው ዋጋ መለወጥ፤ ማሻሻል ወይም ውድድሩን ትቻለው ቢል በጨረታው አጠቃላይ ልዩ ውል መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡ እንደአስፈላጊነቱ መ/ቤቱ ወደ ፊት በሚያውጣው ጨረታ ላይ እንዳይሳተፍ ሊደረግ ይችላል።
10. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ የሆኑባቸው ግዥዎች ላይ ባቀረቡት ዋጋ ብቻ ቤታችን ማስረከብ አለባቸው።
11. ጨረታውን በሚመለከት ጨረታውን ለማሸነፍ እንዲረዳ ለማንኛውም ለኃላፊ እና ሠራተኛ መደለያ ወይም ጉቦ የሰጠ ተጫራች ከጨረታው የሚሰረዝና አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ የሚሰረዝ እና ተጠያቂ የሚሆን መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል።
12. የጨረታው ሠነድን በሚመለከተው መ/ቤቱ ባቀረበው መስፈረት መሠረት መሆን ይኖረበታል።
13. ተጫራቾች የተጫረቱበትን የጨረታ ማስከበሪያ በምድብ የተላያየ ሲሆን በዚህ መሠረት ደንብ ልብስ፤ 50,000 ሺህ ሞተር ሳይክል፤ 50,000 ሺህ ሸራተን ወንበር፤ 30,000 ሺህ የመኪና ጎማ፤ 30,000 ሺህ ዱንኳን፤ 20,000 ሺ ብር/በባንክ በተረጋገጠ cpo ከዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
14. ተጫቾች የጨረታው ሠነድን ይህ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ጨረታ መሽጫ ቦታ በተዘጋጀለት ቦታ በስልክ ደውሎ በአካል በመምጣት መግዛት የሚችሉ ሲሆን የመጫረቻ ሠነዱን ከላይ በተገለጸው ቦታ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖረባቸዋል።
15. ጨረታው በ16ኛውን ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሠዓት የሚከፈት ሆኖ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ በበዓል ወይም በእረፍት ቀን ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት የሚዘጋና የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀረብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
16. አሸናፊ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ቢድ ቦንድ ያሸነፉትን ግዥ አጠናቅቀው ካስረከቡ ቦኋላ መልሰው መውሰድ የሚችሉ ሲሆን የጨረታው ተሸናፊዎች ለጨረታው ያስያዙት ቢድ ቦንድ በጨረታው መሸነፋቸውን የሚገልፅ በደብዳቤ እንዲደረሳቸው መረከብ ይችላሉ።
17. በዚህ የተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን ያለመፈፀም በተራ ቁጥር 13 ላይ የተመለከተውን የጨረታ ማስከበሪያ ሊያስቀጣ ይችላሉ።
18. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፉባቸው ግዥዎችን ውል በተገባበት በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ በኡራ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡ ውል በተገባ ጊዜ ውስጥ ማስረከብ ያልቻለ በውል ላይ በተቀመጠው መሠረት ተጠያቂ ይሆናል።
19. ለአሸናፊው ድርጅቶች ክፊያው የሚፈፀመው ውል የተገባላቸው ንብረትቶች በተራ ቁጥር 18 ላይ ያሉትን ግዴታዎች ከተወጣ ቦኃላ ይሆናል።
20. የተፈቀደው የግንኙነት ዜዴ በስልክ ሲሆን ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ 09-17-89- 92-80 የኡራ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ደውሎ መጠይቅ ይችላሉ።
21. ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ በአግባቡ ካነበቡትና አስፈላጊውን መረጃ ከሞሉ በኃላ በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም ተመቶበተ ከፖስታው ጋር ታሽገው መመለስ ይኖርባቸዋል።
22. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
23. ጨረታው ከተዘጋ ቦኃላ የሚቀረብ ማንኛውም የጨረታ ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
24. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘ ዋስትና በጨረታው ለተሸነፉ ድርጅቶች ወዲያውኑ የሚመለስ ሲሆን አሸናፊ ድርጅቶች ግን ያሸናፉበትን ንብረት ካስረከቡ ቦኃላ የሚመለስላቸው ይሆናል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኡራ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-07
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-10-07 10:30
- Region: Beneshangul Gumuz
- Publishing entity: Ura Woreda FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 22, 2026)
- Posted at: 2026-09-22T11:32:58.000Z
- Source: 2merkato