Other Sales

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ወረዳው በተለያዩ ጊዜ በግዥ፤ በዕርዳታና በስጦታ ያገኟቸው ያገለገሉ ንብረቶችን ማለትም ያገለገለ መኪና፣ የውሃ ቱቦ ባለብረት የተለያየ ኢንች፣ የሞተር ሳይክሎች፣ ቆራሌ ብረቶች እና ሌሎች ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ወረዳው በተለያዩ ጊዜ በግዥ፤በዕርዳታና በስጦታ ያገኟቸው ያገለገሉ ንብረቶችን ማለትም ያገለገለ መኪና፣ የውሃ ቱቦ ባለብረት የተለያዬ እንች፣ የሞተር ሳይክሎች፣ ቆራሌ ብረቶች እና ሌሎች ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-

1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች ዝርዝር ጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለዶክመንቱ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ሥራ ሂደት /ክፍል/ በመውሰድ ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ አንድ ኦሪጂናልና አንድ የኦሪጂናል ኮፒ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከገዙ በኃላ ከጨረታው ቀን በፊት ንብረቶቹን በአካል ለማየት ይችላሉ።

4. የጨረታው አሽናፊ ማሸነፉ እንደተረጋገጠ ያሸነፉትን ዋጋ በኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ መደበኛ አካውንት ሙሉ በሙሉ ገብ ስያደረግ ያሸነፈውን ንብረት ወዲያኑ ይረከባል፡፡ ሌሎች ዝርዝር ሂደቶች በጨረታ ሰነዱ የሚካተቱ ይሆናል።

5. የመኪና እና ሞተር ተሽከርካሪዎች ስም ዝውውር በገዥ ይሸፈናል፤ የተሽከርካሪዎች ታርክ ማስረጃ መ/ቤቱ ለገዥው ያቀርባል። ሌሎች ንብረቶች የይሰፊ ደብዳቤ ይሰጣል።

6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናቶች ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ በ 16ኛው ሥራ ቀን ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 5፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት/ባይገኙም/ ይከፈታል፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09-16-59-96-57/ 09-16-35-11-13/ 09-25-14-75-81 ይደውሉ፤

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-23
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናቶች ቅኦይቶ በ16ኛው ሥራ ቀን ከቀኑ 5፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-23 11:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናቶች ቅኦይቶ በ16ኛው ሥራ ቀን ከቀኑ 5፡30 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Wolaita Zone Bayira Koysha Woreda FEDB
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 07, 2026)
  • Posted at: 2026-11-07T07:44:17.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders