Disposal Sale
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ሰነድ ቁጥር 132
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ቁሳቁሶቹም፡-
- ቁርጥራጭ አልሙኒየም (ስክራፖች)
- ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችና ቶቦላፊዎች /ስክራፕ/
- ያገለገሉ ጎማዎችና የፍሬን ዘይት
- ያገለገሉ ሶፋዎች
- ያገለገሉ የስፕሪንግ ፍራሾች
- የውሃ ጀሪካኖች
- ያገለገሉ ወንበሮች
- የውሃ ታንከሮች
- ብዛት ያላቸው የኢንዶንዥያ ምርት የሆኑ ውድ ፍሪ ወረቀቶች ባለ 80 ግራም እያንዳንዱ ሪም 500 Sheet የያዙ ወረቀቶች
በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾ አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03፣ (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም ከጠበል መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት) በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ቁሳቁሶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ከተመለከቱ በኋላ በማዕከሉ የጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ድረስ በመምጣት ብር 400 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
የጨረታ ሰነዱ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ቁሳቁሶች ዝርዝር የያዘ ሲሆን፤ ዕቃዎቹን እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ በሰነዱ በእያንዳንዱ ቁጥር አንፃር የተለዩትን ዕቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት እና ዕቃውን ለመግዛት ያስገቡትን ዋጋ 10% ለጨረታ ማስከበሪያ ከያዘ ሲ.ፒ.ኦ ጋር በማያያዝ ካሸጉ በኋላ የጠቅላላ አገልግሎት ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ኛው ቀን እሁድ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡-
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፦ 0989-90-90-51 ወይንም 0975-26-41-59 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-11-17
- Bid closing time: 10:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-17 11:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ5፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Mekedonia Charity Association
- Buyer TIN: 0027054421
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 400 (አራት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Nov 07, 2026)
- Posted at: 2026-11-07T08:41:43.000Z
- Source: Qelal Tenders