Metal and Metal Working

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-1 እና 3 ስኳር ፋብሪካዎች ያገለገሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ክፍል አንድ

የሚወገዱ ንብረቶች ሽያጭ

የመጀመሪያ ዙር የወጣ ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አሽጨ/ዐዐ1/ኦኩስፋ/1 እና 3/2019

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-1 እና 3 ስኳር ፋብሪካዎች ያገለገሉ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ፣ የተለያዬ ያገለገለ ባለ ክር እና ባለ ሺቦ ጎማዎች ፣ የተለያዬ መጠን ያላቸው የተቆራረጡ ከመነዳሪዎች ፣ የተለያዬ መጠን ያላቸው ያገለገሉ የተሽከርካሪና የማሽነሪ ባትሪዎች ፣ ባዶ ያገለገሉ የዘይትና ግሪስ በርሜሎች ፣ ያገለገለ/የተቃጠለ ዘይት (በበርሜል) ፣ ባዶ የአፈር ማዳበሪያ ከረጢት UREA&NPS ፣ የኬሚካል ጀሪካን ባለ 1 ሊትር እና ባለ 5 ሊትር ፣ የኤሲ ጋዝ ባዶ ሲሊንደር ባለ 45 ቁጥር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

1. ማንኛውም ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ስነድ ጋር ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይም ህጋዊ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ስነድ/መረጃ ማቅረብ አለባቸው።

2. ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶች የሚገኙበት አድራሻ፡- ክልል በምእራብ ኢትዮጵያ ቤንች ማጂ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ እና ክልል ደቡብ ኢትዮጵያ፤ ወረዳ ሳላማጎ ወረዳ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር-1 ስኳር ፋብሪካ ግቢ ነው።

3. ጨረታው በቀን 9/03/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል። ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ፖስታ) በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል። በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን: 9/03/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።

4. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00 ከሰዓት በኃላ ከ7፡30-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00) ከታች በተራ ቁጥር-5 እና 6 በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

5. ለሽያጭ የቀረቡ እቃዎች ወይም ንብረቶችን ዝርዝር የያዘው መደበኛ የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት፤ የመወዳደሪያው ሰነድ የሚገባበት እና ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ፡- ኦሞ ኩራዝ ቁጥር -1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ ወደ አየር ጤና በሚወስደው ቶታል ሶስት ማዞርያ ወደ ተዘንአ አጠቃላይ ሆስፒታል በሚያስገባው አስፓልት የፊደራል ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ ነው። ስልክ ቁጥር 09-63-44 28 82 A 09-13-54 47 31 አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ!

6. ለሽያጭ የቀረቡ ዕቃዎች ርክክብ የሚፈፀመው ቦታ በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ግቢ ውስጥ ነው።

7. ጨረታው ጸንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30(ሰላሳ) ቀናት ነው።

8. ብቁ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ጥቅል ዕቃዎች ቀጥሎ የተመለከተውን የብር መጠን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡-

  • ሎት- 1 ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ሽያጭ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
  • ሎት-2 ያገለገለ ባለ ክር እና ባለ ሺቦ ጎማዎች ሽያጭ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
  • ሎት-3 የተቆራረጡ ከመነዳሪዎች ሽያጭ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
  • ሎት-4 ያገለገሉ የተሽከርካሪና የማሸነሪ ባትሪዎች ሽያጭ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር)
  • ሎት-5 ባዶ ያገለገሉ የዘይትና ግሪስ በርሜሎች ሽያጭ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
  • ሎት-6 ያገለገለ/የተቃጠለ ዘይት (በበርሜል) ሽያጭ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር)
  • ሎት-7 ባዶ የአፈር ማዳበሪያ ከረጢት UREA&NPS ሽያጭ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር)
  • ሎት-8 የኬሚካል ጀርካን ባለ 1 ሊትር እና ባለ 5 ሊትር ሽያጭ ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)
  • ሎት-9 የኤሲ ጋዝ ባዶ ሲሊንደር ባለ 45 ቁጥር ሽያጭ ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)

ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-1 እና 3 ስኳር ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-18
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-11-18 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Sugar Industry Group
  • Buyer's registered address: ካሳንቺስ ፣ ከንግድ ሚኒስቴር በስተቀኝ ገባ ብሎ ጆሴፍ ቲቶ መንገድ ከኪያሜድ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ሕንፃ በስተጀርባ የሚገኘው 4ኛ ፎቅ ላይ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 07, 2026)
  • Posted at: 2026-11-07T09:17:44.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders