Stationery

የቢፍቱ ከተማ አስተዳደር በሥሩ ለሚገኙ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የእንስሳት መድኃኒት እና ሞተር ሳይክል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የቢፍቱ ከተማ አስተዳደር በስሩ ለሚገኙ ሴ/መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የጽ/መሳሪያ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የእንስሳት መድሀኒት ሞተር ሳይክል በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፦

1. ተጫራቾች ለመወዳደር የሚያስችል በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣

2 ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣

3. በአቅራቢነት የተመዘገቡበት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ

4. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን፣

  • ለጽ/መሳርያ ብር 50,000 ሃምሳ ሺህ ብር/
  • ለእንስሳት መድሀኒት 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/
  • ለኤሌክትሮኒክስ ብር 50,000/ሃምሳ ሺህ ብር/
  • ለፈርኒቸር ዕቃ ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/
  • ሞተር ሳይክል 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ

5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የቢፍቱ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ዩኒት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን።

6. የተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የቢፍቱ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ዩኒት ቢሮ ቁጥር 6 ማቅረብ ይኖርባችኋል።

7. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ ታሽጎ በ16 ቀን በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ በዓላት ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።

8. በጨረታ ያሸነፋቸውን ዕቃዎች የቢፍቱ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ዩኒት ድረስ የሚያቀርቡ ይሆናል።

9. የጨረታው አሸናፊዎች አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን ዕቃዎች አጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከመ/ቤታችን ጋር የግዥ ውል ስምምነት መፈጸም ይኖርባቸዋል።

10. መስሪያ ቤቱ የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ

  • ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ በጥራትና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በተባለው ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

አድራሻ ፡- የቢፍቱ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ዩኒት

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09-17-27-02-83

የቢፍቱ ከተማ አስተዳደር


Tender details

  • Deadline: 2026-11-24
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-24 14:30
  • Bid opening (note): የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን እስከ 8፡30 ሰዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: ቢፍቱ ከተማ አስተዳደር
  • Bid bond: ለእያንዳንዱ ሎት 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Nov 06, 2026)
  • Posted at: 2026-11-06T08:54:31.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders