Textile, Garment and Leather
የአፍሪካ አንድነት ቁ.2 አጸደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት አመት የተለያዩ በሎት ምድብ የተከፋፈሉ አጠቃላይ እቃዎች እና የጥገና ስራዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Textile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsTextile, Garments and Uniforms
Addis Ababa
More tags
Printed Advertising MaterialsAdvertising and PromotionPrinting and PublishingMedical Equipment and SuppliesHealth Care, Medical IndustryHealth Related Services and MaterialsPharmaceutical ProductsMaterialsEducation and TrainingCleaning and Janitorial Equipment and ServiceEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsHand Tools and Workshop EquipmentComputer and AccessoriesIT and TelecomConstruction Machinery and EquipmentConstruction and Water WorksTransportation ServiceWarehousing, Transit and Transport ServiceFreight TransportHouse and BuildingMaintenance and RepairOthersOffice Machines and AccessoriesOffice Supplies and ServicesStationeryBuilding and Finishing MaterialsOffice Machines and ComputersVehicleRentBuilding ConstructionFinishig WorksAmharic2merkatoAfrica Andenet No.2 Kindergarten & Elementary School
Description
የመጀመሪያ ዙር የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር አፍ/አን/ቁ.2/አጸ/ህጻ/የመ/ደ/ት/ቤት/01/2019 ዓ.ም.
የአፍሪካ አንድነት ቁ.2 አጸደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት አመት የተለያዩ በሎት ምድብ የተከፋፈሉ አጠቃላይ እቃዎች እና የጥገና ስራዎች ማለትም
- ሎት 1 የደንብ (የስራ ልብስ)
- ሎት 2 (አላቂ የቢሮ እቃዎች)
- ሎት.3 የህትመት
- ሎት 4 አላቂ የህክምና እቃዎች
- ሎት 5 (አላቂ የትምህርት እቃዎች)
- ሎት 6(አላቂ የጽዳት እቃዎች)
- ሎት 7(ልዩ ልዩ መሳሪያዎች)
- ሎት.8 (ለፕላንት ማሽነሪ መሳሪያዎች መግዣ)
- ሎት 9(ለህንጻ ቁሳቁስና ተገጣጣሚ እቃዎችና)
- ሎት 10 (የተለያዩ ለፕላንት ማሽነሪ ጥገና)
- ሎት 11 ለትራንስፖርት (ለጭነት)
- ሎት 12 ለልዩ ልዩ ክፍያዎች እንደሁም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ት/ቤቱ መግዛት እና ማስጠገን ይፈልጋል።
ስለሆነም ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባችኋል።
- በዘርፉ የተሰማሩና ጊዜው ያላለፈበት የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዘጋቢ ስለመሆናቸው እንዲሁም ከላይ የተጠቀሱትን ዝርዝር ሰነዶችን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የንግድ ምዝገባ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ከላይ በሎት ምድብ የተጠቀሱትን እቃዎች ዝርዝር የተካተተበት የግዥ የግልጽ ጨረታ መመሪያን የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በት/ቤት ውስጥ በሚገኘው የካሸር ቢሮ ቁጥር 4 በመግዛት መውሰድ ይችላሉ። እንዲሁም ለጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ካደራጃችሁ አካል የምታመጡት ደበብዳቤ በምን ዘርፍ እንደተደራጃችሁ የሚገልጽ ደብዳቤ ማምጣት ይኖርባችኋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያገለግል የሚወዳደሩበትን የእቃዎች ማለትም ለሎት 1፡- 10000 ብር ለሎት 2፡-10000 ብር ለሎት 3፡- 3000ብር ለሎት 4፡- 3000 ብር ለሎት 5፡- 5000 ብር ለሎት 6፡- 5000 ብር ሎት 7፡- 4000 ብር ሎት 8፡- 5000 ብር ሎት 9፡ - 6000 ብር ሎት 1ዐ፡- 10000 ብር ለሎት11፡- 5000 ብር ለሎት12፡ 3000 ብር በት/ቤቱ ስም ከታወቀ ባንክ የተዘጋጀ ሲፒኦ በማስያዝ ማረጋገጫውን ከሚወዳደሩበት ሰነዶችጋር ማስገባት ይኖርባችኋል።
- እንዲሁም የጨረታው አሸናፊ ከሆኑ ደግሞ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ለውል ማስከበሪያ የጠቅላለው ዋጋ የሚሆን 10% ውል ሲዋዋሉ ማስያዝ ይኖርባችኋል፡።
- ተጫራቾች ለጨረታ የሚያስፈልጉ ሰነዶች እና የእቃዎችን ዝርዝር ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ውስጥ በክፍል 4 ውስጥ በሚገኘው የዋጋ መሙያ ዝርዝር ላይ የአንዱ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም(ቫት) ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላት የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት በአፍሪካ አንድነት ቁ.2 አጸደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ ለዚሁ ጨረታ ሰነድ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ የሚወዳደሩበትን አጠቃላይ ሰነዶች ላይ ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት የድርጅታችሁን ክብ ማህተም በማድረግ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባችኋል።
- ተጫራቾች አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችሉም።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለሁሉም እቃዎች የቅርብ ጊዜ ምርት(ጊዜው ያላለፈበት ምርት) ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባችኋል። እንዲሁም ናሙና ለማቅረብ የሚቸገሩባቸውን እቃዎች በፎቶ የተደገፈ ጥራት ያለ ምስል ያለው ፎቶ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባችኋል።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛ የስራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ ከሆነ ከረፋዱ 5፡00 ሰአት ታሽጎ በእለቱ 5፡30 ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በት/ቤት ውስጥ በሚገኘው የግዥ ክፍል ውስጥ ይከፈታል።
- ት/ቤቱ የተሻለ የግዥ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ የት/ቤቱ አድራሻችን ፡- አበበች ጎበና ህጻናት መርጃ አጠገብ ወይም ዩሀንስ ቤ/ክርስቲያን አካባቢ በሚገኘው አቤት ሆስፒታል ሲደርሱ ወደ ውስጥ በሚያስገባው ኮብል ስቶን ገባ ብሎ ነው።
ለበለጠ መረጃ የት/ቤቱ ስልክ ቁጥር (011-157-2591) ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የአፍሪካ አንድነት ቁ.2 አጸደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-03
- Bid closing time: 11:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛ የስራ ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰአት
- Bid opening: 2026-10-03 11:30
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛ የስራ ቀን በእለቱ 5፡30 ሰአት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Africa Andenet No.2 Kindergarten & Elementary School
- Buyer address: አበበች ጎበና አጠገብ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 22, 2026)
- Posted at: 2026-09-22T11:47:38.000Z
- Source: 2merkato