Printing and Publishing

የሮቤ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ለሁለተኛ ጊዜ ግዥ በከተማው ስር ላሉ መ/ቤቶች የተለያዩ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስጠገን ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የሮቤ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት የ2019ዓ.ም በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ለሁለተኛ ጊዜ ግዥ በከተማው ስር ላሉ መ/ቤቶች የተለያዩ ህትመቶች የስፌት ዋጋ የከባድ እና ቀላል መኪና ጥገናዎች፣ የኤሌትሮኒክስ ጥገናዎች፣ የማሽነሪ እስፔር ፓርቶች የከተማ ማስዋቢያ ችግች እና የችግኝ ዘሮች አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስጠገን ይፈልጋል።

ስለዚህ በዘርፉ ፍቃድ ያላችሁ ተወዳዳሪዎች እዲካፈሉ እየጋበዝን በዉድድሩ ላይ ለመሳተፍ ቀጥሎ የቀረቡትን መመዘኛዎች ወይም መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅበታል።

1.ቲን ነምበር /Tin No እና VAT ተመዝጋቢ መሆናችሁን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችል።

2.ህጋዊ 2019 የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈላችሁበትን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችል፡፡

3. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ኮፒዉን ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ የሚችል፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመግዛት ሮቤ ከተማ ገ/ጽ/ቤት ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች የዕቃውን /Brand Name / መሙላት አለባቸው፡፡

6. የጨረታውን ሠነድ ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ዋናዉንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

7. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት 11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት የጨረታው ሠነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ ከታሸገ በኋላ በዛው ዕለት 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል።

8. የጥገና፤ ህትመቶች፤ እና የማሽነሪ እስፔር ፓርቶች፣ የከተማ ማስዋቢያ ችግኞች፣ ስፌት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50000 (ሃምሳ ሺህ ብር በባንክ የተረጋገጠ በሲፒኦ ብቻ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

9. የዕቃዎቹን ዋጋ መ/ቤቱ የሚከፍለዉ ንብረቱ ሙሉ በሙሉ ንብረት ክፍል ገቢ ሆኖ በጥያቄው መሠረት መቅረቡ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።

10. ዕቃዎቹ ገቢ ሆነው ገንዘብ ከተከፈለ በኋላ ለአላቂ ዕቃዎች የ6 ወር ለቋሚ ዕቃዎች የı ዓመት ጊዜ ጋራንት/ዋስትና መስጠት የሚችልና ዕቃዎቹ የተበላሹና ኦርጅናል ካልሆኑ ለመመለስ ግዴታ የሚገባ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም ናሙና ማቅረብ የሚችል ሲሆን ሠነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።

11. ተጫራቾች ያሸነፉባቸዉን ዕቃዎች የማጓጓዣ፣ ማስጫኛና ማዉረጃ ወጭውን በመቻል ሮቤ ከተማ ገ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. ለበለጠ መረጃ ሮቤ ከተማ ገ/ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 0934866474/0912365294 መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የሮቤ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-03
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት 11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-03 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት 11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Robe City Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 22, 2026)
  • Posted at: 2026-09-22T12:35:45.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders