Sport Materials and Equipment

የኢትዮጵያ ትቅደም ቁ.1 ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2019 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ትቅደም ቁ.1 ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በመንግስት መደበኛ በጀት በተገኘ ገንዘብ በቂ አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት /1/ የስራተኛ ደንብ ልብስ፣
  • ሎት 2/የእስፖርት ትጥቅ
  • ሎት 3 የስፖርት እቃዎች፣
  • ሎት 4/ የደንብ ልብስ ስፌት፣
  • ሎት 5/አላቂ የቢሮ እቃዎች
  • ሎት/6/ አላቂ የጽዳት እቃዎች፣
  • ሎት/ 7/ልዩ ልዩ መሳሪያዎችና መጻህፍት
  • ሎት/8/የትምህርት አላቂ እቃዎች፣
  • ሎት/9/አላቂ የህክምና እቃዎች
  • ሎት/10/የህትመት ስራዎች፣ 
  • ሎት 11 ከቋሚ እቃ ኤሌክትሮኒክስ፣
  • ሎት/12/ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶች ጥገና፣
  • ሎት/13/ ማሽነሪ ጥገና፣
  • ሎት /14/ቋሚ እቃ ፈርኒቸር
  • ሎት15/ የህንጻ ቁሳቁስ እቃዎች በዚህ መሰረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡

1. በሙያው ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል እና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡

2. በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምዝገባ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ፡፡

3. በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የዚህን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ተራ ቁጥር ላይ የተቀመጠዉን መስፈርት ሲያሟሉ ብቻ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ በየሎት ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር ቀን ጀምሮ ቢሮ ቁጥር 04 መውሰድ ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች ጨረታ ማስከበሪያ የሚያገለግል ለቋሚ እቃ በየሎት ብር 15,000.00(አስራ አምስት ሺ ብር) እና ለሌሎች አላቂ እቃዎች በየሎት ብር 8,000.00 (ስምንት ሺ ብር )በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. ተጫራቾች በሚወደደሩበት አላቂ እና ቋሚ እቃ ሳንፕል በአይነት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

7. ተጫራቾች በሚወደደሩበት ቋሚ ትልልቅ እቃዎች ሳንፕል በፎቶ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናት ውስጥ የሚያቀርቡትን ዋጋ በክፍል አራት፤ ስድስት እና ዘጠኝ ላይ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ ዋና እና ኮፒ በት/ቤቱ ፋይናንስና ግዢና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡

9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት በየሎት የጨረታ ስነድ ዋናውንና ኮፒውን በተናጠል በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

10. የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት ታሽጎ ከጠዋቱ 3፡30 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 04 ይከፈታል፡፡

11. የጨረታ አሸናፊ ድርጀቱ ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት እና ወዛደር የት/ቤቱ ንብረት ክፍል 2ኛ ፎቅ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

12. ዋጋው ፀንቶ የሚቆየው አሸናፊው ከተለየበት ቀን አንስቶ ለ6ዐ ቀናት ይሆናል፡፡

13. በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ በሚያመርቱት ምርት ከሆነ ሰነዱ በነጻ የሚወስዱ ሲሆን በማያመርቱት ምርት ላይ ሰነድ · ይኖርባቸዋል፡፡

14. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡

15. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ጨምቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

16. ተጫራቾች ባሸነፉበት የእቃ ርክክብ የሚደረግበት ሰዓት 2፡30 እስከ 10፡30 ማምጣት ይኖርባቸዋል፡፡

17. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡ ልዩ ቦታ ከሰሜን ሆቴል ከፍ ብሎ ከዜና አገልግሎት በስተጀርባ ዶሮ ተራ

በስልክ ቁጥር፡- ዐ111-71-22-00 እና ዐ111-55-07-24 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የኢትዮጵያ ትቅደም ቁ.1 ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-03
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት
  • Bid opening: 2026-10-03 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰአት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopia Tikdem No.1 Kindergarten, Elementary & Middle School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Sep 22, 2026)
  • Posted at: 2026-09-22T12:39:30.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders