Stationery

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ አስተዳደር የሠላም በር ቅድመ አንደኛ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን እና ስራዎችን በጨረታ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መመሪያ መ.ቁ 02/19

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ አስተዳደር የሠላም በር ቅድመ አንደኛ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ እቃዎችን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ በዘረፉ የተሠማራችሁ ህጋዊ ነጋዴዎችን በጨረታ አወዳድረን በቴክኒክና እና በዋጋ በማወዳደር አሸናፊ ከሆኑት ድርጅቶች ለመግዛት የምንፈልግ መሆኑን እናሳውቃለን ፡፡

  • ሎት.1 አላቂ የፅህፈትና የቢሮ እቃዎች
  •  ሎት2. የፅዳት እቃዎች
  •  ሎት3.የደንብ ልብስ
  •  ሎት4. የህትመት ስራዎች
  • ሎት 5.ቋሚ እቃዎች
  • ሎት 6 የማእከል እቃዎች ና የተለያዩ መጽሃፍቶች
  • ሎት 7. የቤተ ሙከራ እቃዎች
  • ሎት8. የኤሌክትሮኒክስና የኮምፒውተር ጥገና ስራዎች

 ፡- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሠ የንግድ ፍቃድ መሆኑን የሚገልፅ አግባብነት ያለው ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባወጣው የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር እና በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ከሰአት 7፡30- 11፡30 የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ በሠላም በር ቅድመ አንደኛና የመጀመሪያ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ክፍያና ሂሳብ አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት በመቅረብ የማይመለስ 300 ብር /ሶስት መቶ ብር ከፍለው መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. እስከ 10ኛው ቀን ድረስ የእቃዎችን ዝርዝር ዋጋ እና አይነት በመግለፅ በታሸገ ፖስታ ከአንድ ኮፒ ጋር በግዢ ቢሮ በተዘጋጀወ ሳጥን ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  4.  የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል ፡፡(ተጫራቾች ቢግኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል)
  5. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የሚያቀርቡት የእቃ አይነት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበት፣ስልጣን ባለው አካል የተፈረመባቸው የተሟላ አድራሻቸውን የሚገልጽና ህጋዊ ማህተብ ያረፈበት ሊሆን ይኖርበታል፡፡
  6.  ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚያቀርቡት እቃዎች በሙሉ ናሙና ወይም ሳምፕል ማቅረብ፣ የፕሪንተር ቀለሞች እና ኮምፒተር እና የአሌክትሮኒክስ እቃዎች ኦርጅናል ትክክለኛነት/ የማረጋገጫ ዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO/ ሎት1.14000 ሎት.2.12000 ሎት.3.000 ሎት.4.800 ሎት5. 6000 ሎት6.1000 ሎት7.600 ሎት8.900 በት/ቤቱ ስም በማሰራት ከጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሠዓት በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸው አካል የጨረታ ማስከበሪያ ደብዳቤ በት/ቤቱ ስም ማለትም ሠላም በር ቅድመ አንደኛ & የመጀመሪያ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በሚል አፅፈው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ የዋጋ ለውጥም ሆነ ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም በተወዳደሩት ዋጋ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በ (7)ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርበው የውል ማስከበሪያ 10% ለግዥ ፈፃሚ አካል ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው በውል መሠረት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ከተወጡና ውሉን ተመላሽ ሲያደርጉ ነው፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለጸበት በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል ካልተዋዋለ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
  11. በጨረታው ያሸነፉ ተጫራቾች ለአሸነፉአቸው ዕቃዎች ውል ከተዋዋሉበት ቀን ጀምሮ በአስር ቀን ውስጥ በራሳቸው የትራንስፖርት ፣የማስጫኛ እና የማስወረጃ ወጪ በመክፈል ለሠላም በር ቅድመ አንደኛና የመጀመሪያ ደረጀ ት/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል ፡፡ እቃዎቹን ገቢ የማያደርጉ አሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የውል ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡ በተጨማሪ በግዥ መምሪያ መስረት በህግ የሚጠየቁበት ስርዓት እንፈጥራለን፡፡
  12. ት/ቤቱ አሸናፊው ተጫራች ከመረጡ በኋላ በሚገዙት እቃዎች ብዛት መጠን ላይ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 20% የመቀነስ ወይም የመጨመር መብታቸው የተጠበቀ ነው ፡፡
  13. ተጫራቾች  በጨረታው አፈፃፀም ሂደት ቅሬታ ካላቸው በግዥ አዋጅ ቁጥር 649/2001 አንቀፅ 51፣53 እና 54 እንዲሁም በመንግስት ግዥ አዋጅ አፈጻፀም መመሪያ አንቀፅ 43 መሠረት አቤቱታ የማቅረብ መብታቸው እንደተጠበቀ ነው፡፡
  14. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. በጨረታው ሰነድ ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዮች ካሉ ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 7 የስራ ቀናት ውስጥ በአካል በመቅረብ ሠላም በር ቅድመ አንድኛ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ግዥ ቢሮ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  16.  ት/ቤቱ ባዘጋጅው ቅፅ ወይም የዋጋ ማቅረቢያ በስተቀር በሌላ ቅፅ መሙላት አይቻልም፡፡
  17. ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅፁን ሲሞላ 15 %ቫትን በማካተት ይሆናል፡፡ 15% ቫትን ያላካተተ ተጫራች ለውድድር አይቀርብም፡፡

አድራሻ፡- በኮልፌቀራኒዮ ክ/ከተማወረዳ 10 ሉካንዳ ታክሲ ማዞሪያ ወደ ፌደራል ፖሊስ

ማስልጠኛ ተቋም በሚወስደው አስፓልት በስተ ቀኝ በኩል ሰዋሰው ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ጎን

ስልክ ቁጥር. 0112739095/0112739030.

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ አስተዳደር የሠላም በር ቅድመ አንደኛ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-03
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-03 10:30
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ 11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ሰላም በር ቅድመ አንደኛ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 22, 2026)
  • Posted at: 2026-09-22T12:41:08.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders