Equipment and Accessories

በደ/ኢ/ክ/መ/ የኮንሶ ዞን የካራት ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፐላን ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በካራት ከተማ አስተዳደር ሥር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 

በደ/ኢ/ክ/መ/ የኮንሶ ዞን የካራት ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፐላን ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በካራት ከተማ አስተዳደር ሥር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች

  • የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ፤
  • የፈርኒቸር ግዥ፤
  • የአላቂና ሌሎች አላቂ
  • የቢሮ የጽ/መሣሪያ ዕቃዎች ግዥ፣ 
  • የስፖርት ትጥቅ ግዥ ፤
  • የፋብሪካ ውጤቶች የግንባታ ቁሳቁስ ግዥ እና
  • የሞተር ሣይክል ግዥ

 በግልጽ ጨረታማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ በጨረታው ላይ ለመወዳደር ለምትፈልጉ

ተጫራቾች /ድርጅቶች፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው ።
  2. በዘርፉ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው።
  3. በዘርፉ/TIN Number/የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ያላቸው።
  4. በዘርፉ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ያላቸው።
  5. በዘርፉ የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው።
  6. በዘርፉ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ያላቸው።
  7. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታዉን ሠነድ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15/አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዘርፍ የዕቃው ዓይነት ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 800 /ስምንት መቶ ብር ብቻ/ በኮንሶ ዞን ካ/ከ/አስ/ር ገ/ባ/ቅ/ጽ/ቤት ገቢ አሰባሰብ ዋና የሥራ ሂደት ከፍለው ደረሰኝ በመያዝ በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ር ዋና ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር - 6 በመቅረብ ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  8. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
  9. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 30,000 /ሠላሳ ሺህ ብር ብቻ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ፤ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና፤ የተረጋገጠ ቼክ፣ CPO ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክረዲት ከቴክኒካል ኦርጅናል መረጃዎች ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  10. በሁሉም ዘርፍ ላይ መወዳደር የምትፈልጉ ዕጩ ተጫራቾች የዕቃው ዝርዝር የያዘና ቴክኒካል ሰነድ ብቻ ለብቻ በአንድ አንድ ኤንቨሎፕ የሚቀርብ ሆኖ ቴክኒካልና ፋይናንሻል እያንዳንዳቸው አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ማለትም ቴክኒካል ኮፒ፣ ኮፒ-2 እና ፋይናንሻል ኮፒ-1፣ ኮፒ 2፣ ቴክኒካል ኦርጅናል -1 እና ፋይናንሻል ኦርጅናል -1 በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በቴክኒካል ኦርጅናል ውስጥ በማስገባት በትከክል በማሸግ፤ የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ፣ ስም፤ ፊርማ እና አድራሻ በመግለጽ በየዘርፉ ስድስት ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  11. የጨረታው ሣጥን የሚታሸገው በ16ተኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሲሆን የሚከፈተው በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  12. ጨረታው ይከፈታል በተባለበት በ16ኛው ቀን በመንግስት የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  13. አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ ሰነድ 10% እና ተመጣጣኝ የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ይዘው ቀርበዉ ውል ባይገቡ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዘው ብር 30,000 /ሠላሳ ሺህ ብር/ ለመንግስት ውርስ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።
  14. በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት በውሉ መሠረት አቅርቦቱን በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ለመ/ቤታችን ማስረከብ ይኖርበታል።
  15.  ተጫራቾች ተሟልተው ያለመገኘት የጨረታው አከፋፈት ሥነ-ሥርዓትን አያስተጓጎልም።
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- /09-76-14-36-45 /09-20–98–00–30/09-00-69-71-33/ 09 13-89-17-79 ላይ ደውለው ያግኙን፤

በደ/ኢ/ክ/መ/ የኮንሶ ዞን ካራት ከተማ አስ/ር/ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-09
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-09 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው የሥራ ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Konso Zone Karat City Administration Finance Office
  • Bid bond: 30,000 ብር
  • Bid document price: 800.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Sep 22, 2026)
  • Posted at: 2026-09-22T13:40:56.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders